
“ሌሎች በኢትዮጵያ የሚገኙ ዞኖች ሰኔ ሲመጣ ወር ላይ የተሰጠን በጀት ጨርሰናል፤ ድጎማ ይሰጠን ብለው ያገኛሉ ፤ እኛ ለዚህ አልታደልንም ያሉ ሲሆን ምንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ብናልፍም በክብራችን እና በማንነታችን ለገንዘብ ስንል አንደራደርም” ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ_ የዞኑ ምክትል አሰትዳዳሪ እና የዞኑ የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 17/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በበጀት መነፈግ የሚቀየር ማንነት በወልቃይት ጠገዴ የለም! ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 17/ 2015 ዓ.ም. በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወፍአርግፍ ከተማ የወረዳው አስተዳደር ያሰራው ህንፃ የዞኑ ምክትል አሰትዳዳሪ እና የዞኑ የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሐላፊ ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በተገኙበት ተመርቋል። የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ክብረአብ ስማቸው በዕለቱ እንደተናገሩት ፤ ይህ ህንፃ ምንም በጀት ባልተመደበለት ዞን አመራሩ የውሎ አበሉን በመሰረዝ ነዋሪው ደግሞ ያለውን ሁሉ እየሰጠ በወኔና በእልህ የተሰራ ቤት ነው ያሉ ሲሆን ፤ እንዲሁም በውጭ የሚገኙ የወልቃይት ጠገዴ የዲያስፖራ ማህበረሰብ ለህንፃው መጠናቀቅ ያበረከቱት አስተዋፅኦ የሚያስመሰግን ነው ብለዋል። አቶ ገ/እግዚአብሔር ደሴ የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሐላፊ በበኩላቸው ፣ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ለሌሎች አርአያ የሚሆን ፅናትን የታደለ የማይበገር አማራ ነው፤ በዚህም እንኮራለን ብለዋል። በመጨረሻም የዕለቱ የክብር ዕንግዳ ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ሌሎች በኢትዮጵያ የሚገኙ ዞኖች ሰኔ ሲመጣ ወር ላይ የተሰጠን በጀት ጨርሰናል፤ ድጎማ ይሰጠን ብለው ያገኛሉ ፤ እኛ ለዚህ አልታደልንም ያሉ ሲሆን ምንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ብናልፍም በክብራችን እና በማንነታችን ለገንዘብ ስንል አንደራደርም ብለዋል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በበጀት መከልከል ምክንያት ማንነቱን ይቀይራል ማለት የማይታሰብ ነው ! ምንጭ_የወልቃይት ጠገዴ ሰ/ሁመራ ብልጽግና
Source: Link to the Post