
ሌ/ጄነራል አበባው ታደሰ ከግንባሩ የጦር አዛዦች ጋር በመሆን የከሃዲውን የትሕነግ አመራሮችን መቆጣጠር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መምከራቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሽብር ተግባር የተሰማራው የትሕነግ ቡድን አመራሮችን ለመቆጣጠር በሚቻልበት ጉዳይ ነው ሌ/ጄነራል አበባው ታደሰ ከግንባሩ የጦር አዛዦች ጋር መምከራቸው የተገለፀው፡፡ ሌተናል ጀነራል አበባው ታደሰ በመቀሌ ከተማ ነው ከጦር አዛዦቻቸው ጋር ስለመምከራቸው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በይፋዊ ገጹ አስታውቋል። በትግራይ በተወሰነ አካባቢ ላይ ቀደም ብለው ባዘጋጁት ጉድጓድ የተደበቁትን ከሀዲዎች አድኖ በቁጥጥር ስር ለማዋል በሚያስችል ዝርዝር ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ነው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የገለፀው፡፡
Source: Link to the Post