You are currently viewing ልባዊ ምስጋናዬ ከአክብሮት ጋር ይድረሳችሁ!! ሞላ ፈለቀ (ዶክተር ) ============================== እኛ ኢትዮጵያውያን ባሕልና ወግ ሆኖብን ሰውን በሕይወት እያለ የሚገባውን…

ልባዊ ምስጋናዬ ከአክብሮት ጋር ይድረሳችሁ!! ሞላ ፈለቀ (ዶክተር ) ============================== እኛ ኢትዮጵያውያን ባሕልና ወግ ሆኖብን ሰውን በሕይወት እያለ የሚገባውን…

ልባዊ ምስጋናዬ ከአክብሮት ጋር ይድረሳችሁ!! ሞላ ፈለቀ (ዶክተር ) ============================== እኛ ኢትዮጵያውያን ባሕልና ወግ ሆኖብን ሰውን በሕይወት እያለ የሚገባውን ክብር ሰጥተን ማመስገን አለመደብንም። እኛ ኢትዮጵያውያን ለጀግና በሕይወት ዘመኑ ተገቢውን ድጋፍ ሰጥተን ይበልጥ እንዲጀግን ከማድረግ ይልቅ ጠልፈን ለመጣል ብዙ ርቀት በመሄድ እንታወቃለን። ይህ የእኛ ትውልድ ግን ይህንን ባሕል ተሻግሮና ከፍርሃት ቆፈን ተላቆ በሕይወት ዘመኑ ለጀግና ተገቢውን ክብር በመስጠት አእላፍ ጀግኖች እንዲፈጠሩ ማድረግ ይጠበቅበታል። የሆነው ሆኖ “የኮሚሽነር አበረ አዳሙ ማስታዎሻ” የሚለውን መጽሐፍ ስናዘጋጅ ሐሳብ ያዋጣችሁ፣ መረጃና ማስረጃ ያቀረባችሁ፣ ስለኮሚሽነር አበረ አዳሙ ግለሰብዕና እና የነጻነት ተጋድሎ የጽሑፍ ምስክርነት የሰጣችሁ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የሥራ ባልደረቦቹ፣ ወዳጆቹና የትግል አጋሮቹ እንዲሁም የቅርብ ቤተሰቦቹ ያለ እናንተ ተሳትፎ መጽሐፉ በዚህ መልክ ተዘጋጅቶና ተሰንዶ ለትውልድ አይተላለፍም ነበርና ክብርና ምስጋና ይገባችሗል። የዘመናችን አርበኛ የሆነው የኮሚሽነር አበረ አዳሙን 1ኛ ሙት ዓመት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ ግለታኩን የያዘው የማስታወሻ መጽሐፍ የምረቃ መርሐግብር በደማቅ ሁኔታ እንዲካሄድ ያደረጋችሁና ለመርሐግብሩ ስኬት የበኩላችሁን አስተዋፅኦ ያበረከታችሁ አካላት በሙሉ በሰማዕቱ አርበኛ ሥም ልባዊ ምስጋናዬ ከአክብሮት ጋር ይደረሳችሁ። የመጽሐፍ ምረቃ መርሐግብሩን ለመታደም ከሩቅ ውቅያኖስ አቋርጣችሁ የመጣችሁ የአርበኛው የቅርብ ወዳጆች፣ ከቅርብ የመጣችሁ የትግል አጋሮቹ፣ ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹ፣ ምሁራን፣ በመጽሐፉ ላይ አስተያየት ያቀረባችሁ የአማራ ሕዝብ የቁርጥ ቀን አመራሮችና ምሁራን ጊዜያችሁን መስዋዕት አድርጋችሁ በመገኘታችሁ በራሴና በመርሐግብሩ አዘጋጆች ሥም ምስጋናዬ እንዲሁ ይድረሳችሁ። በመጨረሻም ብዙዎቻችን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ለትግል ተፈጥሮ፣ በትግል ኖሮና በትግል የተሰዋ መሆኑን ሳናውቅ፣ አውቀን ሳናግዘው የቀረ፤ በጥልቅ የአገር ፍቅር ተለክፎ ስለአገር ፍቅር ሕይወቱ ያለፈ የዘመናችን አርበኛ ከመሆኑም በላይ አድርባይነትን ተፀይፎና ንቆ በሰዋዊ ልዕልና ያለፈ ኢትዮጵያዊ ጀግና መሆኑን ስመሰክር በኩራት ነው። #ጀግናን_መፍጠርና_ማጀገን_ማኅበረሰባዊ_እሴታችን_ሊሆን_ይገባል!! #ነጻነት_የማያቋርጥ_ትግል_ነው!!

Source: Link to the Post

Leave a Reply