#ልብን የሚመግብ ደም ስር ጥበት ወይም መዘጋት በሽታ (acute coronary syndrome)ይህ በሽታ ደም ወደ ልብ ጡንቻ አንዳይፈስ በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንስ የበሽታ አይነትነው፡፡ስለዚ…

#ልብን የሚመግብ ደም ስር ጥበት ወይም መዘጋት በሽታ (acute coronary syndrome)

ይህ በሽታ ደም ወደ ልብ ጡንቻ አንዳይፈስ በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንስ የበሽታ አይነትነው፡፡
ስለዚህ በሽታ እንዲነግሩንም የልብ እስፔሻሊስት ሀኪም ከሆኑት ከዶ/ር አብዱሰመድ አደም ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡
ልብን የሚመግብ ደም ስር ጥበት ወይም መዘጋት (acute coronary syndrome) የተለያዩ አይነቶች እንዳሉት ባለሙያው ይናገራሉ፡፡
በእንግሊዝኛ አጠራራቸውም
– Stable angina
– Unstable angina
– Non-ST –elevation myocardial infarction
– ST-elevation myocardial infarction ይባላሉ፡፡

#መንስኤዎቹ

– የደም ግፊት
– የስኳር በሽታ
– የኮሊስትሮል መብዛት
– ማጨስ
– የስራ እና የኑሮ ጫና

#ምልክቶቹ

ምልክቶቹ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያለሆኑ ምልክቶች እንደሆኑ ባለሙያው ያስረዳሉ

#ከቀጥተኛ ምልክቶቹ መካከል

– ደረትን ጨምቆ መያዝ እና ደረት ላይ ትልቅ ነገር እንደተቀመጠ መሰማት
– ደረት መውጋት
– ስሜቱ ወደትከሻ እና ወደ እጅ መሄድ
– አንዳንድ ሰው ላይ ደግሞ ወደአንገት እና ድድ እንደሚሄድም ዶክተር አብዱሰመድ ይናገራሉ፡፡

#ቀጥተኛ ያልሆኑ ምልክቶች
– የጨጓራ አካባቢ ህመም
– ተውከት
– ትንፋሽ ማጠር
– የልብ ድካም ይዞ መምጣት

#በሽታው እንዳይከሰት መከላከያ መንገዶች

– የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ
– ጭንቀት መቀነስ
– ሱሶችን ማሰወገድ
-የኮሊሰትሮል መድሃኒታቸውን በአግባቡ ወስዶ ለመቀነስ መሞከር እንደሚጠቀሱበት ባለሙያው ተናግረዋል።

በሃመረ ፍሬው

የካቲት 09 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply