ልብ የሚሰብር ዜና – የለውጥ ሐዋርያው የታንዛንያው ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ በ61 ዓመታቸው አረፉ።ሙስናን ለመዋጋት ተዓምር ሰርተዋል።፣ታንዛንያ ከምዕራብ ኩባንያዎች ጋር የገባችውን የማዕድን ውል ሀገሪቱን በሚጠቅም መልክ እንዲቀየር እየተጋደሉ ነው ያረፉት።አፍሪካዊ መሪዎቻችንን እናክብር! እንጠብቅ!

ለምዕራባውያን የማዕድን ኩባንያዎች የራስ ምታት ነበሩ።ለታንዛንያ መድሃኒት ነበሩ።በአጭር ጊዜ ተአምራዊ የተሰኘ ለውጥ አምጥተዋል።የስም ማጥፋት ዘመቻ በውጭ ሚድያዎች ተካሂዶባቸዋል።የ”ዎል ስትሪት” ድረ-ገፅ ከሰዓታት በፊት የዕረፍት ዜናቸውን የዘገበበት ርዕስ አነጋጋሪ ነው።”ከማዕድን ኩባንያዎች ጋር ውዝግብ የገቡት የታንዛንያው ፕሬዝዳንት በ61 አመታቸው አረፉ” ይላል። ይህ ርዕስ በራሱ የታንዛንያው ፕሬዝዳንት ምን ያህል ለምዕራብ ኩባንያዎች የራስ ምታት እንደነበሩ፣ለታንዛንያ ደግሞ ሩቅ አሳቢ እንደነበሩ አመላካች ነው። ስለ ፕሬዝዳንቱ ሸገር ራድዮ የዛሬ ሶስት ዓመት በመቆያ ፕሮግራም ያቀረበውን እስከመጨረሻ ያድምጡ።****

Source: Link to the Post

Leave a Reply