ልክ እንደመጋዘኑ እህል ስቃጠል አደርኩ! ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ቻግኒ ራንች ካምፕ ያሉት…

ልክ እንደመጋዘኑ እህል ስቃጠል አደርኩ! ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ቻግኒ ራንች ካምፕ ያሉትን ተፈናቃዮች አይቻቸዋለሁ ::ለመጀመሪያ ጊዜ ወደእዚያ ያቀናሁት ካሜራ ይዤ ለስራ አልነበረም ::ይልቁን አለን የተባለው የበጎ ፈቃደኞች ስብስብ ያሰባሰቡትን ገንዘብ እንዴት ማድረስ ይቻላል ምን ያህል ናቸው ምን የበለጠ ያስፈልጋቸዋል የሚለውን ለማወቅ ነበር። እዚያ ስደርስ በአየሁት ነገር ግን ልቤ ተሰበረ በጣም ብዙ ነፍሰ ጡሮች የሚያጠቡ እናቶች የህፃናቱ ቁጥርማ ተዉት ለየትኛው ቅድሚያ ሰጥጥቶ የትኛውን መተው ይቻላል የምንለይበት መንገድ ሁሉ ጨነቀን። ተፈናቃዮቹ ያሳዝናሉ የከተማ ሰው ባዩ ቁጥር ብሶታቸውን ይተነፍሳሉ። የምታመጡት እርዳታ ወደ መጋዘን ይገባል እንጂ ለእኛ አይደርሰንም እንደውም እየወጣ ሲሸጥ በአይናችን እያየን ነው ይሄንን ለጠየቋቸው ሚዲያዎች በመናገራችን ከካምፑ የተባረሩም እንዳሉ ነግረውኛል። መጋዘኑ ውስጥ አቆይተው የተላ ዱቄት ይሰጡናል እሷን በወንፊት ለይተን ነፍሳችንን እናቆያለን። ህፃናቶቹ ልብ ያንሰፈስፋሉ፤ የሚያልፍ የሚያገድመውን ሰው እጅ እየያዙ ምግብ ይጠይቃሉ ለሁሉም መስጠት አለመቻል እንዴት እንደሚያም። የእርዳታ አስባባሪዎቹ ተፈናቃዮቹን የጎሪጥ ነው የሚያያቸው ከማንም ሰው ጋር ሲያወሩ ሰላይ አዳማጮችን ይልኩባቸዋል። እኛም እንድናደርስ የታዘዝነውን ምግቦች እና የመመገቢያ ቁሳቁሶች ካምፕ ውስጥ ካሉት ይልቅ በየሰው ቤቱ እና በየሜዳው ላስቲክ ወጥረው ለሚገኙ ለማድረግ ወስነን ከሶስት ቀበሌዎች(መንታ ውሃ ይማሊ እና አዲስ አለም) በቤተሰብ ቁጥር ለይተን ለተፈናቃዮቹ በቀጥታ እናደርሳለን ስንል ከወረዳው ባለስልጣን እስከ እርዳታ አስተባባሪዎቹ ዘራፍ አሉ መጋዘን ገብቶ እኛ በለየነው መሰረት ካላመናችሁን ባላችሁበት ይሰጣል እንጂ ሞተን ነው ቆመን አሉ ምን ሲደረግ እኛ ሳንበላለት ይመስላል። እዚህ ጋር ምን ትዝ አለኝ አንዲት ወዳጄ የሰው ፊት አይቷት ከጓደኞቿ ጋር የሰበሰበችውን ምግብና ልብስ መጋዘን አስገቢና ልንሰጥ ስንል እንጠራሻለን ከዛ እያየሽ ይሰጣል ብለዋት ብትጠብቅ ብትደውል ማን ሰምቷት አሁን መቃጠሉን ስትሰማ ምን ብላ ይሆን? እርግጥ ነው እኛ ከእልህ አስጨራሽ ንትርክ እንግልት እና እስር በኋላ አድካሚም ቢሆን በቦታው ተገኝተን ያመጣነውን ነገር ሁሉ በቀጥታ ለተጎጂዎች አድርሰናል ፊታቸው ላይ ብርሃን እና ተስፋን አይተናል ያሰሩን ሰዎች ሳይሆን ተስፋ አድርገው የሚጠብቁን ሰዎች አሁንም አይኔ ላይ አሉ። ይሄ ጉዳይ ከእርዳታ መሰብሰብ ባለፈ ከፍ ያለ ስራ ይጠይቃል ሰዎቹ ግፍ እንደማይፈሩ በግልፅ እያሳዩን ነው ጉዳቸው እንዳይጋለጥ ሆዳቸውን ሞልተው በትራፊያቸው እንኳን ድሃው ረሃቡን እንዳያስታግስ አንደውበታል ተስፉቸውን አቃጥለውታል። ነገ ካምፑን እንደማያነዱት ምንም ማረጋገጫ የለንም!

Source: Link to the Post

Leave a Reply