ልዩ ልዩ ፕሮግሞችን ምክንያት በማድረግ ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ልዩ ልዩ ፕሮግራሞችን ምክንያት በማድረግ በመዲናዋ ርችት መተኮስ  የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ አንዳንድ ግለሰቦችና ተቋማት ልዩ ልዩ ፕሮግሞችን ምክንያት በማድረግ ርችት እየተኮሱ መሆኑን ጠቁሞ÷ በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ካለችበት የፀጥታ ሁኔታ በምንም አይነት ምክንያት ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን ገልጿል።
ይህንን መልእክት በመተላለፍ ርችት ሲተኩስ የተገኘ ግለሰብ በህግ የሚጠየቅ መሆኑን ፖሊስ ኮሚሽኑ በአጽንኦት አሳስቧል፡፡
ህብረተሰቡ ለኮሚሽኑ ስራ ስኬታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ÷ሕግን የማስከበር ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጿል።
ህብረተሰቡ ለህግ መከበር እያደረገ ላለው ቀና ትብብር ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቦ ትብብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማስተላለፉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

The post ልዩ ልዩ ፕሮግሞችን ምክንያት በማድረግ ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply