ልዩ መረጃ የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ከኃላፊነታቸው ተነሱበኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ውብሸት አበራ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቀ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/U83S0FUtBV4Qu00KRTycl3zuyOKX1I1HW1wWquyTHMt8dCVITqZQaW-3vJW0x3L9jgw6aDvCuM7B0s279QbtKQDV9uCzbfPY46BQhUeVW4HzxzLY49LH-xmNa2X_qAfdSM5RoDGG2QZ38UoU1IJSpKgNQTw_XItwRWDuG91hHXpPIqbHy5CLUesMpoA7RiuO_2td1jbPTX2h8IPxW_rEmNfxzEFjHSsK1Y_rY8su0FRm0AchV0ThN3FCIKjEAK-dhB_C92ZWQiqQAeSwjfQlu5dg7rBfvaHMVBVK5OCSQiC6zWCm4Kz0nW0OhxMkXUnW_LRpEyu1n6dvAj_Uneq21Q.jpg

ልዩ መረጃ

የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ከኃላፊነታቸው ተነሱ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ውብሸት አበራ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቀዋል።

አቶ ውብሸትን ተክተው አቶ ሺበሺ አያሌው የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው መሾማቸውን ሰምተናል ።

ከባለፈው እሁድ ጀምሮ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በደራ ወረዳ ጥቃት እያደረሰ መሆኑን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል ።

የሽብር ቡድኑ በወረዳው የገጠር ቀበሌዎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ንፁሃንን እንገደለም ታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም ቤት አቃጥሏል፣ ንብረት አውድሟል እንዲሁም ህፃናትና እናቶችን ጭምር ማገቱም ተሰምቷል ።

የታገቱትን ለማስለቀቅም ለአንድ ሰው እስከ 5 መቶ ሺህ ብር መጠየቃቸውን ነዋሪዎቹ ነግረውናል ።

አሸባሪው ሸኔ የወረዳዋን ዋና ከተማ ጉንዶ መስቀልን ለመቆጣጠር ጥቃት እያደረሰ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ሳላይሽና ጬካ የተባሉ ከተሞችን መቆጣጣሩን ወረዳው አስታውቋል።

የጉንዶ መስቀል ከተማ ነዋሪዎችም ከፍተኛ ጭንቅ ውስጥ መሆናቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል ።

ከአዲስ አበባ በ 2 መቶ 20 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የደራ ወረዳ ከባለፈው አንድ አመት ጀምሮ በአሸባሪው ሸኔ ጥቃት እየደረሰባት እንደሚገኝ ይታወቃል ።

በአባቱ መረቀ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply