ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በትግራይ ክልል በተካሄደው ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር  ባደረጉት ድንቅ ተጋድሎ ልባዊ ኩራት እንደተሰማቸው በሰሜን አሜሪካ ቴክሳስ የአማሪሎ ከተማ ነዋሪዎች  ገለጹ፡፡…

ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በትግራይ ክልል በተካሄደው ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር ባደረጉት ድንቅ ተጋድሎ ልባዊ ኩራት እንደተሰማቸው በሰሜን አሜሪካ ቴክሳስ የአማሪሎ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡…

ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በትግራይ ክልል በተካሄደው ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር ባደረጉት ድንቅ ተጋድሎ ልባዊ ኩራት እንደተሰማቸው በሰሜን አሜሪካ ቴክሳስ የአማሪሎ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ አሻራ ሚዲያ ጥር፡-14/05/13/ዓ.ም ባህር ዳር የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በትግራይ ክልል በተካሄደው ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር ባደረጉት ድንቅ ተጋድሎ በሰሜን አሜሪካ ቴክሳስ አማሪሎ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በሰሜን አሜሪካ ቴክሳስ የአማሪሎ ከተማ ነዋሪዎች በትግራይ ክልል በተካሄደው ሕግና ሥርዓት የማስከበር ርምጃ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ባደረጉት ድንቅ ተጋድሎ ልባዊ ኩራት እንደተሰማቸውም ገልፀዋል፡፡ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የአማራ ማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት ብቻ በአምባገነኑ ትህነግ አፈና፣ ስደት፣ እስራትና ግድያ ሲፈፀምባቸው የኖሩ የወልቃይት ጠገዴና የራያ አማራዎች ከነበረው ጭቆና እንዲላቀቁ ልዩ ኃይሉና ሚሊሻው የማይተካ አስተዋፅኦ አበርክቷል ብለዋል፡፡ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በተግባር ላስመሰከሩት የሀገር አለኝታነት 205 ሽህ 975 ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለፃቸውን በሰሜን አሜሪካ ቴክሳስ ሀገረግዛት የአማሪሎ ከተማ ነዋሪዎች ለአብመድ በላኩት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply