ልዩ ወጪ በተመለከተ መመርያ ባለመኖሩ ምክንያት ባለስልጣናት የሀገር እና የህዝብ ሀብት እያባከኑ ናቸው ተባለ። በዚህም የገንዘብ ሚኒስትር የባለስልጣናት ልዩ ወጪ በተመለከተ መመርያ እንዲያዘ…

ልዩ ወጪ በተመለከተ መመርያ ባለመኖሩ ምክንያት ባለስልጣናት የሀገር እና የህዝብ ሀብት እያባከኑ ናቸው ተባለ።

በዚህም የገንዘብ ሚኒስትር የባለስልጣናት ልዩ ወጪ በተመለከተ መመርያ እንዲያዘጋጅ ተጠይቋል።

የህዝብ ተወካይ ምክር ቤት አባላት የመንግስት መስራቤቶች ያለመመርያ የሚያባክኑት የህዝብ እና የሀገር ሃብት ለመቆጣጠር የገንዘብ ሚኒስትር መመርያ ማዘጋጀት አለበት ተብሏል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እንደተናገሩት ያለምንም ተጨባጭ ምክንያት ሚኒስትር መስራቤቶች እና ባለስልጣናት የሀገር ሀብት እያባከኑ ናቸው ብለዋል።

ያለመመርያ እና ህግ ይህንን በሚያደርጉ ሀላፊዎች ላይ እርምጃ መውሰድ አግባብ አይደለም ያሉት አባላቶቹ ሚኒስትር መስራቤቱ መመርያ እና ህግ እንዲያዘጋጅ ጠይቀዋል።

የመንግስት መስራቤቶች ልዩ ወጪ በማለት የሚያወጡት ልክ እንደ ፕርቶኮል ለሹፌር እንደዚሁም ሌሎች ወጪዎች ሀገርን እየጎዱ ናቸው ብለዋል።

እነዚህን አላግባብ የሚወጡትን ወጪዎች ለመቆጣጠር ደንብ እና መመርያ ያስፈልጋል ሲሉ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ተናግረዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 24 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply