ልጄስ? የተሰኘ ተከታታይ ድራማ በካናል ፕላስ ላይ ለእይታ ሊቀርብ ነው::አንድ አባት የጠፋበትን ልጁን ፍለጋ የሚያሳልፈውን ጉዞ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ልጄስ የተሰኘ ተከታታ ድራማ ሊጀምር መ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/JTrg3mg3AUn-IXuT_eIOOO4Qe7vfxQpDmK8lh7yGracFnwBGbRioxeEslQB9Vy6jWvqQoANHerZcXHcG_hg3qK1xfYehiCpckB_4adyN_5ndaI0BygWkW463VCEgdjWNtiurdzR8wnRIyW3U-ihWsKEnBt9nwlQWNJcjgqByWImcx3i7NPJwhwMcePCyz1Scpg7VLWqQTzzomjg4g0GYQ9-X6VYKTli2thOh1hSKyw1OFRsWE4JLHxLVLtMq4BUPcqoF4OQ_cntSoxUm6si1ADBGJyrLAU0-FHOmO0A11Q4wqD9rMv11GFrYrjxaDf7YcEmQHSPLyGQ34FhMKebogw.jpg

ልጄስ? የተሰኘ ተከታታይ ድራማ በካናል ፕላስ ላይ ለእይታ ሊቀርብ ነው::

አንድ አባት የጠፋበትን ልጁን ፍለጋ የሚያሳልፈውን ጉዞ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ልጄስ የተሰኘ ተከታታ ድራማ ሊጀምር መሆኑ ተነግሯል።

ልጄስ የተሰኘው ድራማ አንድ አባት ለልጁ ሲል የሚከፍለውን መስዋዕትነት እና ፍቅር የሚያሳይ ልብ አንጠልጣይ ይዘት እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

በድራማው ላይ አርቲስት ዳንኤል ተሾመ በመሪ ተዋናይነት የተሳተፈበት ሲሆን፤ ከመጋቢት 28 ቀን 2016 ጀምሮ ቅዳሜ እና እሁድ ምሽት 1 ሰዓት በካናል ፕላስ 2 ላይ ይተላለፋል ተብሏል።

ልጄስ የተሰኘው ድራማ ለተከታታይ 42 ክፍሎች ለእይታ የሚቀርብ ሲሆን፤ የ30 ደቂቃ ቆይታ እንዳለው የድራማው ጸሃፊና ዳይሬክተር ሰማኝጌታ አይችሉህም ተናግረዋል፡፡
የተከታታይ ድራማው ቀረጻ 7 ወራትን ጊዜ መውሰዱ የተገለጸ ሲሆን፤ ሙሉ ቀረጻው ከአዲስ አበባ ውጪ መደረጉም ተጠቁሟል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply