
ልጅ ቢኒ እና ፓስተር ቢኒያም ሽታዬ ፍ/ቤት ቀርበው ለፊታችን አርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጧቸዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ልጅ ቢኒ እና ፓስተር ቢኒያም ሽታዬ የካቲት 4/2015 አንድ ላይ ከታሰሩበት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዝቅ ብሎ ከሶርአምባ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው አራዳ ፍ/ቤት ቀርበዋል። ፖሊስ ተለዋጭ ቀጠሮ ያስፈልገኛል በማለቱ ችሎቱ የ7 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ ለፊታችን አርብ ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ እንዲቀርቡ አዟል። ምንጭ_ያያ ዘልደታ ያሬድ
Source: Link to the Post