ሐረር ለዘመናት የምትታወቅባቸው መቻቻልና የመተባበርን የመሰሉ እሴቶች ጎልተው እንዲወጡ ይሰራል- አቶ ኦርዲን

ሐረር ለዘመናት የምትታወቅባቸው መቻቻልና የመተባበርን የመሰሉ እሴቶች ጎልተው እንዲወጡ ይሰራል- አቶ ኦርዲን

አዲስ አበባ ፣ ጥር 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረር ክልል ለዘመናት የምትታወቅባቸው የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመቻቻል ፣ የመተባበር ፣ የመከባበር ፣ የእህትማማችነትና ወንድማማችነት ጠንካራ ማህበራዊ ትስስር ከመቼውም ግዜ በላይ ጎልተውና ልቀው እንዲወጡ የክልሉ መንግስት ቁርጠኛ አቋም ይዞ ለተግባራዊነቱ በመረባረብ ላይ እንደሚገኝ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ  ተናግረዋል።

በሐረሪ ክልል በ2013 ዓ.ም በተከናወኑ የጸጥታ ስራዎች ለጸጥታ ሃይሎች ፣ ለሀይማኖት ተቋማት ፣ ለሰላም ቤተሰብ ፣ ገለልተኛ አማካሪ ቡዱን እና ለሰላም አምባሳደሮች የምስጋና ፕሮግራም ተካሄዷል።

በፕሮግራሙ ላይ በክቡር እንግድነት የተገኙት የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ባስተላለፍት መልዕክት የታሪክ የስልጣኔ የቅርስ ፈርጥ የሆነችው ሐረር ከተማ ለዘመናት የምትታወቅባቸው ጠንካራ ማህበራዊ ትስስሮች ጎልተው እንዲወጡ ይሰራል ብለዋል።

የጸጥታ ዘርፍ እርስ በእርስ በመናበብ ህዝብን በስፋት በማሳተፍ የሚያደርገው መጠነ ሰፊ ውጤታማ ርብርብ በተጨባጭ የሚታየው ለውጥ ለሌሎችም ዘርፎች በአርአያነት የሚጠቀስ የሚደነቅና የክልሉ መንግስት እውቅና የሚሰጠው መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ ያለው ሰላምና መረጋጋት ቀጣይነት እንዲኖረውና ዘላቂ እንዲሆን የሁሉንም እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን ከክልሉ ሰላምና ደህንነት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ ለጀመረችው የአንድነት ፣የእኩልነትና የጋራ ብልፅግናን የሚረጋገጥ የለውጥ ሂደት የሰላም መስፈንና የህግ የበላይነት መከበር መተኪያ የማይገኝላቸው ቁልፍ ተግባራት መሆኑን ተናግረዋል።

የሀገር መከላከያ ፣ የፌደራል ፖሊስ ፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ፣ የክልሉ ፖሊስ ፣ ሌሎች የጸጥታ አካላት ፣ መንግስታዊ ተቋማት ለሀይማኖት ተቋማት ፣ ለሰላም ቤተሰብ ፣ ገለልተኛ አማካሪ ቡዱን እና ለሰላም አምባሳደሮች  ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ሐረር ለዘመናት የምትታወቅባቸው መቻቻልና የመተባበርን የመሰሉ እሴቶች ጎልተው እንዲወጡ ይሰራል- አቶ ኦርዲን appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply