
ከአስራ አምስት አመታት በፊት በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የኢንትርኔት ባንኪንግ ያስተዋወቀው ህብረት ባንክ፣ አሁን በራሱ የውስጥ አቅም ያበለጸገው የሞባይል ባንኪንግ መተግበርያ ይፋ አድርጓል፡፡
ሕብረት ባንክ ያሻሻለውን የዩኤስ ኤስ ዲ መለያ እና የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በራሱ የውስጥ ሠራተኞች አቅም በመተግበር ቀዳሚ መኾኑን ነው ያስታወቀው።
የህብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ፣ፕሮጀክቱ በራስ አቅም መሠራቱ የውጭ ምንዛሬን ከማዳኑም ባሻገር ባንኩ ወደፊት ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር ለሚያከናውናቸው ሥራዎች ጠንካራ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለብሔራዊ ዲጂታላይዜሽን ስትራቴጂም ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።
አዲሱ የሕብረት ባንክ ሞባይል ባንኪንግ የባንኩን ገጽታ በጠበቀ መልኩ የተለያዩ ዘመናዊ አገልግሎቶችን አካቶ ለደንበኞች ምቹ እና ፈጣን በኾነ ሁኔታ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው ብለዋል፡፡
መተግበሪያው ለሁሉም አይነት የገንዘብ ዝውውር እንደሚሠራ እና ጊዜውን የሚመጥን እንደኾነም ተገልጿል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 01 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን
Source: Link to the Post