ሕብር ኢትዮጲያ ለሶስት  ፓርቲዎች የአብረን እንስራ  ጥሪ አቀረበ። (አሻራ፣የካቲት16/2013 ዓ•ም ባህርዳር) ሕብር ኢትዮጲያ ድሞክራሲያዊ ፓርቲ ለሶስት (3) ፓርቲዎች የአብረን እንስራ ጥ…

ሕብር ኢትዮጲያ ለሶስት ፓርቲዎች የአብረን እንስራ ጥሪ አቀረበ። (አሻራ፣የካቲት16/2013 ዓ•ም ባህርዳር) ሕብር ኢትዮጲያ ድሞክራሲያዊ ፓርቲ ለሶስት (3) ፓርቲዎች የአብረን እንስራ ጥ…

ሕብር ኢትዮጲያ ለሶስት ፓርቲዎች የአብረን እንስራ ጥሪ አቀረበ። (አሻራ፣የካቲት16/2013 ዓ•ም ባህርዳር) ሕብር ኢትዮጲያ ድሞክራሲያዊ ፓርቲ ለሶስት (3) ፓርቲዎች የአብረን እንስራ ጥሪ አቅርቧል ።የኢኃን፣ኢዴፓ እና ህብር የተባሉ ፓርቲዎች ውህድ የሆነው ሕብር ኢትዮጲያ ድሞክራሲያዊ ፓርቲ አብን ፣መኢአድ እና ባልደራስ ጋር አብሮ ለመስራት በደብዳቤ ጠይቋል። 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ምክንያት በማድረግ አብን ፣ባልደራስ እና መኢአድ በአንድ ላይ በመሆን እና በመናበብ አብረው ለመስራት በተግባቡባቸው ጉዳዮች ላይ እየሰሩ እንደሆነ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ ከዚህ በፊትም አብረን እንድንሰራ ስንጠይቅ ቆይተን በመጨረሻ ሳይሳካ ቢቀርም አሁን ባለንበት ሁኔታ ምርጫን በተመለከተ የእጩ መደራረብ እንዳይኖር እና እርስበርስ አለመፎካከርን በተመለከተ አብረን እንስራ ሲል ሕብር ኢትዮጲያ በዛሬው ዕለት በላከው ደብዳቤ ገልፃል። በባልደራስ፣ በአብን እና በመኢአድ በኩል እስካሁን ምንም አይነት ምላሽ እንዳልተሰጠም ለማወቅ ችለናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply