ሕወሃት ድርድሩን የፈለገዉ ለጊዜ መግዣ ነዉ—-አብንየአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ የሚገኘውን ድርድር እንደሚደግፍ አስታዉቋል፡፡…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/iQIGOXOf8M44RNLNop-zB3IeBEg8lc82EcJ_jSB8ef9gQuhUKCQc7npcejL6OEUMX17OVczJJq4M-8TajJRj7bDa2hh1gw-syNh6IUJWkG2fIxncrS77ismyu_23tmLQ1U5oZmJtvQ3ma5QJggjvSdd104DOnz1oxRSK-wwTe-tR1RsYL_cZTS0AxQ-g7LOasCYeehC6ib-fykMKtNQj2IUJYabluJZCiBZN09x7iRUXMVE8LAANJZFOUifC7wrJWnVyPMy0r2tfwnD-9pwgU6wI2ufpaGjjAGrBIJcfeYynplA8yRcNH2K2j0ytQg8MV8RoPS7k3Kqmncb59m4cLw.jpg

ሕወሃት ድርድሩን የፈለገዉ ለጊዜ መግዣ ነዉ—-አብን

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ የሚገኘውን ድርድር እንደሚደግፍ አስታዉቋል፡፡

አብን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ላይ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ መልካሙ ሹምየ እንደተናገሩት፤ መንግስት ከሽብር ቡድኑ ጋር በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት በደቡብ አፍሪካ እያካሄደው ያለውን ድርድር ይደግፋል፡፡

የሽብር ቡድኑ ድርድሩን የተቀበለው ጊዜ ለመግዣ ነው ያሉት አቶ መልካሙ፤ ቡድኑ ለሰላም ድርድር የሚመች ቢሆን ኖሮ እናቶች፣ አባቶችና የሃይማኖት አባቶች ሳይቀር መቀሌ ድረስ በመሄድ ስለ ሰላም ተንበርክከው ሲለምኑት ሳይቀበል፤ የትግራይን ህዝብ ሲጠብቅ የኖረው የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ ክህደት ባልፈጸመ ነበር ነዉ ያሉት።

አቶ መልካሙ ሕወሃት ለሰላም ድርድር የማይሆን ቡድን ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 22 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply