ሕወሓትና ኦነግ በአሸባሪነት መፈረጅ እንዳለባቸው የህግ ምሁራን ጠየቁ፡፡                    አሻራ ሚዲያ             ህዳር…

ሕወሓትና ኦነግ በአሸባሪነት መፈረጅ እንዳለባቸው የህግ ምሁራን ጠየቁ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር…

ሕወሓትና ኦነግ በአሸባሪነት መፈረጅ እንዳለባቸው የህግ ምሁራን ጠየቁ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-23/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር መንግሥት ሕወሓትንና ኦነግ ሸኔን በአሸባሪነት ሊፈርጃቸው እንደሚገባ የሕግ ምሁራን ጠይቀዋል፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባውን ማካሄዱ ይታወሳል፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ እንዲሰጡባቸው ከምክር ቤት አባላት ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል ሕወሓትንና ኦነግ ሸኔን በአሸባሪነት መፈረጅ አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከምክር ቤት አባላት በጉዳዩ ላይ ተደጋግሞ የተነሳው ጥያቄ ተገቢና የሚጠበቅ መሆኑንም የሕግ ምሁራን ተናግረዋል፡፡ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምሕርት ቤት መምህር ተመስገን ሲሳይ እንዳሉት ኢትዮጵያ የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያጸደቀችው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 ሽብርተኝነትን በማያሻማ መልኩ አስቀምጦታል፡፡ የተቀመጡ የሽብር ድርጊቶች በሙሉ በኢትዮጵያ መፈጸመዋቸውንም አቶ ተመስገን ተናግረዋል፤ የድርጊቱ ባለቤት የሕወሓት መሪዎች መሆናቸውንም የመንግሥትን ተደጋጋሚ መግለጫ ዋቢ አድርገው አብራርተዋል፡፡ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ሕግ መምህር ደጀን የማነ እንዳሉት ኦነግ ሸኔ ቦኮሀራም የተባለው የአሸባሪ ቡድን ናይጀሪያ ላይ እንደሚያደርገው የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ካገተ ቆይቷል፤ ንጹኃን ዜጎችን በተለይ ዘርን በመለየት አማራውን አሰቃይቷል፤ ገድሏል፤ ልዩ ልዩ የሽብር ድርጊቶችንም ፈጽሟል፡፡ አቶ ደጀን በሰጡት ማብራሪያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስልጣንና ተግባር ሕግ ማውጣትና ውሳኔ ማሳለፍ ቢሆንም አስፈጻሚ አካላት በጉዳዩ ላይ ቸልተኛ ስለዚህ ሕወሓትና ኦነግ በዓለም ላይ ያለ አሸባሪ የሚሠራውን ሁሉ ሠርተዋል በአሸባሪነት ለመፈረጅም መረጃዎች ከበቂ በላይ ሞልተው ፈስሰዋል ብለዋል፡፡ በሽብር መፈረጅ ግልፅ የሆነ የሕግ መስፈርት እንዳለው በመጥቀስም ሁለቱ ቡድኖች ግን ከዚያ የዘለለ ዓለም አቀፍ የዘር ማጥፋት ወንጀሎችንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸማቸውን አንስተዋል፡፡ መንግሥት በሽብርተኝነት ለመፈረጂ ያሳየው ዳተኝነትም ተገቢ እንዳልሆነ አመላክተዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply