“ሕይወቱን ለሚሰጠን ደም እንስጥ” በሚል መሪ መልእክት የፍኖተ ሰላም ከተማ ነዋሪዎች ደም ለለገሱ ሕዳር 23/03/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም ከተማ አስተ…

“ሕይወቱን ለሚሰጠን ደም እንስጥ” በሚል መሪ መልእክት የፍኖተ ሰላም ከተማ ነዋሪዎች ደም ለለገሱ ሕዳር 23/03/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ነዋሪዎች አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይልን ባለበት ለመቅበር በግንባር እየተዋደቀ ለሚገኘው የሰራዊት አባላት ደም ለገሱ ፡፡ የደብረ ማርቆስ ደም ባንክ አገልግሎትና የምእራብ ጎጃም ዞን የሕለውና ዘመቻ አስተባባሪዎች ባዘጋጁት የደም መስጠት መርሃ ግብር በርካታ ነዋሪዎች የገንዘብና የአይነት ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ደም ለሚያስፈልጋቸው የሰራዊት አባላት ደማቸውንም ለግሰዋል ፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎች ሕይወቱን ለሐገር ክብርና ነጻነት መከበር ለሚገብር ሰራዊት የእኛ ደም መስጠት ትንሹ ስጦታ በመሆኑ በቀጣይም ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን ያሉት ፡፡ … ደም ከመስጠት ባሻገር በማንኛውንም ግንባር ተሰልፈን ለማዋገትና አካባያችንን በመጠበቅ ፣ የዘማች ቤተሰብን በመንከባከብ እና ስንቅ በማዘጋጀት ደጀንነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል ፡፡ የደም ልገሳ መርሃ ግብሩን ከደብረ ማርቆስ ደም ባንክ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የምዕራብ ጎጃም ዞን የህልውና ዘመቻ አስተባባሪ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ መምህሩ ዮናታን ዳኛቸው ማህበረሰቡ የሕልውና ዘመቻው ያስከተለውን ጉዳት ተገንዝቡ ሁለንተናዊ ድጋፉን እንዲያደደርግ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ እየሰሩ ናቸው ፡፡ በወታደራዊ ግንባር እየቆሰሉ በየሆስፒታሉ ያሉ ግጅኖችን ሕይወት ለመታደግ ደም መለገስ አስፈላጊ በመሆኑ ህብረተሰቡ ደም በመለገስ በደም እጥረት የሰው ሕይወት እንዳይቀጠፍ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል ፡፡ የደብረ ማርቆስ ደም ባንክ ኃለፊ አቶ ከፋለ ገበየሁ ደም መለገስ በሚተካ ደም የማይተካ ሕይወት ማትረፍ ነው ፡፡ በተለይ በዚህ ወቅት በግንባር ላሉ የነጻነት ታጋዮች ደም የሚያስፈልግ በመሆኑ ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ ደሙን በመስጠት ለሰራዊቱ ደጀንነነቱን በተግባር እያረጋገጠም ይገኛል ፡፡ በቀጣይም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ፡፡ በዛሬው እለት የከተማዋ የእስልምና እምነት ተከታዮች በተደራጀ መንገድ ደም በመለገስ አለኝታነታቸውን አረጋግጠዋል ፡፡ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply