ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቦንጋ ለመግባት ቢሞክርም በሕዝበ ክርስቲያኑ እና በጸጥታ ኃይሎች ቅንጅት ዕቅዱ መክሸፉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 28 ቀን 2…

ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቦንጋ ለመግባት ቢሞክርም በሕዝበ ክርስቲያኑ እና በጸጥታ ኃይሎች ቅንጅት ዕቅዱ መክሸፉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 28 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በከፋ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙት 12 ወረዳ ቤተ ክህነቶች የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ላይ ሳሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥያቄያችን ካልተመለሰ የካቲት 5 ቀን ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል ብሎ መናገሩን ተከትሎ ለዛሬ የታሰበው ሰልፍ እንዲቀር ነገር ግን ሁሉም በተጠንቀቅ እንዲጠብቅ ተነጋግረው ቆይተዋል። ነገር ግን ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰዓት አካባቢ ሕገ ወጡ ቡድን እየመጣ ነው መባሉን ተከትሎ በቦንጋ ከተማ በአሥሩ አድባራት የሚገኙ ካህናትና ምእመናን በነቂስ ወጥተው የኦሮሚያ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አዋሳኝ ወደ ሆነችው ጎጀብ ወደ ተባለችው ኬላ ደርሰው ከክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ኬላውን ዘግተው በመጠበቅ ላይ ሳሉ ሕገ ወጡ ቡድን ይደርሳል። ሕገ ወጡ ቡድን በኦሮሚያ ፖሊስ ታጅቦ የመጣ ቢሆንም ግር ግር በመፍጠር ለመግባት ቢሞክሩም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊስ፣ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት ከምእመኑ ጋር ሆነው በመከላከላቸው ወደ ጅማ መመለሳቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ወደ ቦንጋ የሚያስገቡ መንገዶች ሁሉ ተዘግተው የመኪና እንቅስቃሴ ቆሟል። ሕዝበ ክርስቲያኑም በከፋ በሚገኙት በአሥሩም አድባራት ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን በመጠበቅ ላይ ይገኛል ሲል ተሚማ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply