
ሕገ ወጡ ቡድን የጭሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን ወረረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 23 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ሕገ ወጡ ተሿሚ ቡድን በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጭሮ ከተማ የሚገኘውን የጭሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ወረራ ፈጽሟል። የሕገ ወጡ ቡድን ተሳታፊዎች በዛሬው ዕለት ጠዋት ላይ የወረዳው ሚሊሻ አጅቧቸው የመቃኞ ቤተ ክርስቲያኑን በር በመስበር መግባታቸው ተገልጧል። የካቲት 21/2015 የአካባቢው ምእመን ሕገ ወጡ ቡድን ወረራ ሊፈጽም መሆኑን ተረድተው ቤተ ክርስቲያኑን ሲጠብቁ በመዋላቸው ሊሳካለት ያልቻለው ቡድኑ የካቲት 22/2015 ምእመናን ወደ ሥራቸው መሠማራታቸውን ተገን አድርጎ መውረሩን ተጠቅሷል። በተጨማሪም ወጣት ማንድራስ የተባለ ኦርቶዶክሳዊ መታሠሩም ተነግሯል። ሕገ ወጡ ቡድን ከዚህ ቀደም የሀገረ ስብከቱን መንበረ ጵጵስናን ጨምሮ ተሽከርካሪዎችንና ንብረቶችን መውሰዱን ከአሁን ቀደም መዘገቡን በማስታዎስ ያጋራው ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል (ተሚማ) ነው።
Source: Link to the Post