You are currently viewing “ሕግ በጉልበተኞች ሰደፍ መሸነፏን በተግባር አሳይተናል፤ መራር ቢሆንም እንታገለዋለን!”        አቶ ስንታየሁ ቸኮል  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…   ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም…

“ሕግ በጉልበተኞች ሰደፍ መሸነፏን በተግባር አሳይተናል፤ መራር ቢሆንም እንታገለዋለን!” አቶ ስንታየሁ ቸኮል አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም…

“ሕግ በጉልበተኞች ሰደፍ መሸነፏን በተግባር አሳይተናል፤ መራር ቢሆንም እንታገለዋለን!” አቶ ስንታየሁ ቸኮል አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ እና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል መልእክት አስተላልፊልኝ ብሏል! ስጠቀምበት የነበረውን የማሕበራዊ ሚዲያ ለመክፈት አስቸጋሪ ስለሆነብኝ አጭር መልዕክት ለወገኖቻችን ማስተላለፍ አልቻልኩም በማለት ለመላው የነፃነት ትግል አጋሮቻችን ከፍ ያለ አክብሮታቸውን ገልፀዋል። ላደረጋችሁት እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ! የአንድ ሰዉ የፍትህ መጓደል የሁሉም እንደመሆኑ መጠን በታሰርኩበት የግፍ እስር ወቅት ድምጽ ለሆናችሁ ከጎኔ ለነበራችሁ አባሎቻችናና ደጋፊዎቻችን በሙሉ እንዲሁም ለሚዲያ አጋሮች እና ለአክቲቪስቶች በአገር ውስጥም በውጭም ላላችሁ ሰዎች ደጋፊዎች ባጠቃላይ ልባዊ ምስጋናዬ በድጋሚ ይድረሳችሁ! በቅርብ ጊዜ ወደ ትግሉ ለመመለስ የግል ሕክምናዬን በማድረግ የጥሞና ጊዜ አስፈላጊ በመሆኑ በድጋሚ እንደምከሰት ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ። ክብር ለፈጣሪ አመሰግናለሁ! አቶ ስንታዬሁ ቸኮል በሶስና ፈቃዱ በኩል ያስተላለፈው መልዕክት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply