ሕግ ወዴት አለህ?—-የመስቀል ተጓዦች
የመስቀል በአል ለማክበር ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመሔድ የተዘጋጁ ተሳፋሪዎች የተጋነነ የታሪፍ ዋጋ እየተጠየቁ እንደሆነ ተናግረዋል።
ለመስቀል በአል በጉራጌ ዞን ለማክበር ወደ ዞኑ እያቀኑ ያሉ ተጓዦች የትራንስፖርቱ ጉዳይ እንዳማረራቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
በአውቶቢስ ተራ ትራንስፖርት ለማግኘት የወጡ በተለይም ወደ ወልቂጤ እና አካባቢው የሚያቀኑ ተጓዦች ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ 200 ብር እንከፍል የነበረው የትራንስፖርት ዋጋ አሁን 1ሺህ 500 ብር እየተጠየቅን ነው ብለዋል።
ይህ ወልቂጤ ከሆነ ብቻ ነው፡ ከዛ ካለፈ ብሩም ይጨምራል ያሉት ተጓዦች፣ በዚህም ከፍተኛ መጉላላት እየገጠማቸው መሆኑን አብራተዋል፡፡
በዚህ መስመር ከዚህ ቀደምም ተደራራቢ ችግሮች የሚስተዋሉበት እንደሆነ የተናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ ተኩረት እንዲሰጠውም ጠይቀዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም ተጓዦች ያቀረቡትን ቅሬታ በተመለከተ የትራንስፖርት ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎችን ለማነጋገር ጥረት ያደረገ ቢሆንም ምላሽ ማግኘት አልተቻለም፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video