መላው የተማሪ ወላጆች፣ ማህበረሰቡ እንዲሁም የአማራ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ  ሲቪክ ማህበራትና ሌሎች አደረጃጀቶች በአማራ ተማሪዎች ቀጣይ እጣፋንታ ላይ በኃላፊነት ስሜት እንዲንቀሳቀሱና የመፍት…

መላው የተማሪ ወላጆች፣ ማህበረሰቡ እንዲሁም የአማራ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሲቪክ ማህበራትና ሌሎች አደረጃጀቶች በአማራ ተማሪዎች ቀጣይ እጣፋንታ ላይ በኃላፊነት ስሜት እንዲንቀሳቀሱና የመፍት…

መላው የተማሪ ወላጆች፣ ማህበረሰቡ እንዲሁም የአማራ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሲቪክ ማህበራትና ሌሎች አደረጃጀቶች በአማራ ተማሪዎች ቀጣይ እጣፋንታ ላይ በኃላፊነት ስሜት እንዲንቀሳቀሱና የመፍትሄው አካልም እንዲሆኑ ጥሪ ቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) በ2011 እና በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኦሮሚያና በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በተነሳ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ከ40,000 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነው መቅረታቸውን በጥናት ማረጋገጡን አስታውቋል። ማህበሩ በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የባለፈው ዓመት ችግር እንዲቀረፍና የተፈናቀሉ ተማሪዎች ወደ መደበኛ ትምህርታቸው እንዲመለሱ በተደጋጋሚ የጉዳዩ ባለቤት የሆኑ ባለድርሻ አካላትን ሲያሳውቅ እንድቅየም አስታውሷል። ሆኖም ጥያቄያችን ችላ በማለት ዩኒቨርስቲዎች ተመራቂ ተማሪዎችን ጥሪ በሚያደርጉበት ወቅት በጥቃት ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑትን አለማካተታቸውን ለአተማ የደረሰዉ መረጃ ስለማመልከቱም ጠቅሷል። እንደአብነትም በ2011ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከቡሌሆራ ዩኒቨርስቲ እና በትግራይ ክልል ዩንቨርሲቲዎች አማራ በመሆናቸው ምክንያት የተፈናቀሉ ከ5,000 በላይ ተማሪዎች መፍትሄ ሳይሰጣቸው እንደተበተኑ መቅረታቸውን አውስቷል። በተጨማሪም በ2012 ዓ.ም የጥቃቱ ሰለባ የሆኑትን 22,000 እና የ12ኛ ክፍል ፈተና ላይ በትምህርት ሚንስተር ስህትት እድላቸው የታጠፈባቸዉን 13,000 ተማሪዎች ጨምሮ በሁለት ዓመት ብቻ ከ40,000 በላይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚገኝ የነበር የአማራ ተማሪ ሙሉ በሙሉ ከትምህርት ገበታ ዉጭ ሆኗል ነው ያለው ማህበሩ በመግለጫው። በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የትውልድ ክስረት ያጋጠመ ነው ያለው አተማ ከአሁን በፊት የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት ተማሪዎች ጉዳይ ዕልባት አግኝቶ አዲስ ወደ እነዚህ ዩኒቨርስቲዎች የሚመደቡ ተማሪዎች በመንግስት ሙሉ ዋስትና እና የሞራል ደህንነት እንዲሄዱ የሚመለከታቸዉ አካላትን ሲወተውት መቆየቱን ገልጧል። ይሁን እንጅ ዩንቨርሲቲዎች ተመራቂ ተማሪዎችን በጠሩበት ወቅት የተፈናቀሉትን አለማካተታቸዉ አሁንም ለጉዳዩ ትኩረት እንደተነፈገዉ ያመላክታል ብሏል። በመሆኑም መላው የተማሪ ወላጆች፣ ማህበረሰብ እንዲሁም የአማራ ጉዳይ ያገባናል የምትሉ ሲቪክ ማህበራትና ሌሎች አደረጃጀቶችም በአማራ ተማሪዎች ቀጣይ እጣፋንታ ላይ በኃላፊነት ስሜት እንድትንቀሳቀሱና የመፍትሄው አካልም እንድትሆኑ ሲል አተማ ጥሪ አቅርቧል። የታገቱ ተማሪዎችን ጉዳይ መንግስት እልባት እስኪሰጥ ድረስ እና በተፈናቀሉ ተማሪዎች ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ ምላሽ እስኪሰጥ ድረስ ጥያቄውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአማራ ተማሪዎች ማህበር አተማ ከጥቅምት 15 እስከ 17 ቀን 2013 ዓ.ም በባህር ዳር ባካሄደው 1ኛ ዓመት አስቸኳይ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ አቋሙን ማሳወቁ ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply