
መላ ሕዝቡን በማንቃትና የንቅናቄውን ትክክለኛ ገጽታ በማሳዬት በኩል የአብን የዞን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች ሚናቸው የጎላ መሆኑ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 5 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ከአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች ለተውጣጡ የንቅናቄው የዞን የሕዝብ ግንኙነት አመራሮች ለሁለት ቀናት በምርጫ ዘመቻና ተያያዥ የአሸናፊነት ክህሎት ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ማግኖሊያ ሆቴል መስጠት መጀመሩን አስታወቀ። መላ ሕዝቡን በማንቃትና የንቅናቄውን ትክክለኛ ገጽታ በማሳዬት በኩል የዞን የሕዝብ ግንኙነት አመራሮች ሚና የጎላ መሆኑን የገለፁት የአብን ሊቀመንበር በለጠ ሞላ ቀጣዩ አገራዊ ምርጫ ለሕዝባችን ያለውን ዘርፈ ብዙ ትርጉም በማስረዳትና አካባቢውን ያገናዘበ የምርጫ ቅስቀሳ ስልት በመንደፍ ምርጫው በአብን አሸናፊነት ዘንድ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። መሰል ስልጠናዎች ተለዋዋጭ የሆነውን የአገሪቱን ፖለቲካ ተረድቶ የሕዝባችንን ኹሉንአቀፍ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ የፖለቲካና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎችን ለመስራት ያግዘናል ያሉት የስልጠናው ተሳታፊዎች ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበ የምርጫ ቅስቀሳ ስልቶችን በመንደፍ ሕዝቡ አብንን እንዲመርጥ እንደሚሰሩም ተናግረዋል። ስልጠናው በቀጣይ ሳምንት አዲስ አበባን ጨምሮ ከክልል ውጭ ላሉ የአብን የዞን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊወች በአዲስ አበባ የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል።
Source: Link to the Post