መልዕክት ለአማራ ልሂቃን ***** (አሻራ ሚዲያ ሐምሌ 2/2014 ዓ.ም ሰሜን አሜሪካ) ከኢህአደግ ምስረታ ጀምሮ እስከ ብልፅግና ድረስ የአማራ ልሂቃን ብዙ ስህተቶችን አዋልደው፣ፈፅመውና የ…

መልዕክት ለአማራ ልሂቃን ***** (አሻራ ሚዲያ ሐምሌ 2/2014 ዓ.ም ሰሜን አሜሪካ) ከኢህአደግ ምስረታ ጀምሮ እስከ ብልፅግና ድረስ የአማራ ልሂቃን ብዙ ስህተቶችን አዋልደው፣ፈፅመውና የዘር ፍጅት ሰለባ እንድንሆን በማድረጋቸው ታሪክ ያስታውሳቸዋል። የአማራ ልሂቃን ግልፅ የመንግስት ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነው አሁን አማራ የሚባል ህዝብ እንድጨፈጨፍና የዘር መጥፋት አደጋ እንድደርስበት የአንበሳውን ድርሻ ወስደዋል። አድርባዮ #ምሁር በህዝባችን ዘንድ ጥሎት ያለፈው ስነ ልቦናዊ ጦስ በዋናነት አማራውን እንደ ህዝብ አዋርድታል፣ክዶታል፣አሳልፎ ሰጥቶታል፣አሁንም በህዝባችን ላይ ልዩ የሆነ ፍላጎት እያስተናገደ ያለው የአማራ ልሂቃን ናቸው። ህዝባችን በእውነትም እጅግ የሚያሳዝን የታሪክ ስብራት ውስጥ ይገኛል። ጀግንነቱን፣እምነቱን፣አስፈሪነቱን እና ሃቀኝነቱን በአመራሮች፣በምሁራን፣በልሂቃኑ የበላይነት ባህሉን አውድመውበታል። የአማራ ህዝብ ሆይ አስተውል!! ወደ ነባር ማንነትህ ተመለስ!! ያስተማርካቸው ልጆችህ ሁሉንም ነገር አምነው ለጠላት አሳልፈው ሰጥተውሃል። ይህንን የዘመናት ጥቁር ጥላሸት ለመመለስ የግደታ የባህል አብዮት ማድረግ ያስፈልጋል። የአማራ ህዝብ በቅርብ ጊዜ እምነቱን፣ማንነቱን፣ስነ ልቦናዊ ታሪኩን ፣ተፋቅሮ መኖሩን ፣ተከባብሮ መኖሩን ጭምር ከአብራክህ የወጡት ልጆችህ ለጠላት አሳልፈው ሰጥተውታል። ታላቁን ህዝብ ያሳነሳችሁ እናንተ የዘመኑ ራስ ወዳዶች ሆይ ታሪካዊ ተጠያቂ ናችሁ። አማራ በየጫካው እንድውድቅ፣ሬሳው እንድጎተት፣በጅምላ እንድቀበር ልዩ የሆነ የዘር ጥፋት አስተባባሪ እና አቀናባሪዎች በመሆናችሁ መሆኑን ያለ ጥርጥር ታውቁታላችሁ። ጊዜ ዳኛ ሆኖ እሰኪመጣ ድረስ የሚሰጣችሁ ፍርድ አይኖር ይሆናል። ነገር ግን የታሪካዊ ጠላቶቻችን አንዱ አካል መሆናችሁን ግን በእርግጠኝነት ሳንናገር አናልፍም። አማራነት፥ ሬሳው እስኪገተት፣ ጅምላ እስኪረሸን፣ ሞቱ ከዛፍ ችግኝ ሲያንስ፣ የዘር መጥፋት አደጋ ሲያጋጥመው፣ በሌሎች ብሔር እና ብሔረሰቦች ሳይቀር እንድጠላ ሲደረግ። መንግስትን ያዳነ ህዝብ ሲከዳ ክልሉ በህግ ማስከበር ስም ሲፈርስ፣ በቀጥታ የዘር ፍጅት ውስጥ እየተደረገበት ያለን ህዝብ እንደት ልታድኑት ነው ያሰባችሁት?? ህዝብንስ በዚህ ደረጃ ማስናቅ ተገቢ ነውን?? የሚገርመው አሁንም #በአብይ አህመድ ያላችሁ መተማመን ደግሞ ሲመረመር ከ 70% በላይ ደጋፊው እናንተ መሆናችሁ። ህዝቡ በአብይ አህመድ ተላላኪዎች እንድህ ስር የሰደደ ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ገብቶ በሁሉም ቦታ ድብታ ውስጥ ሲገባ እናንተ ምንድነው የረዳችሁት?? እውነት ግን የአማራ ህዝብ አያሳዝናችሁም?? በተለይ 01, ፓርላማ ውስጥ ያላችሁ ብልፅግናዎች 02, በአብይ አህመድ ወንበር ስር ያላችሁ አመራሮች 03, የሃይማኖት አባቶች 04,ተዋቂ ሰዎች እንደት እያሰባችሁት ነው?? ይህን ጉዳይ በቀላሉ እየተገነዘባችሁት እንዳላችሁ ግን እናውቃለን። ታላቁን ህዝብ አሳንሶ ስልጣን፣ገንዘብ፣ምቾት እና ሰላምስ ታገኛላችሁ። ለሁሉም አሁንም ተስፋችን አብይ አህመድ ነው የምትሉ ተምራችሁ ነገር ግን ምቾት ያደነቆራችሁ ልሂቃኖች ተውን። ስለ እግዚያብሔር ብላችሁ ህዝባችን አታዘናጉት!! እመኑኝ የወደ ፊቷ ኢትዮጵያ #ኩሺ ናት!! ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ።ህዝባችንንም በጊዜ እናንቃው!! ማህበረሰቡን ያላነቃችሁት እናንተው የቂል ፓለቲከኞች ናችሁ። ም/ቤትን በአርሶ አደር ማዋቀር ምንዓይነት ስሜት እንደሚሰጣችሁ ባላውቅም የክልሉን ህዝብ በማደንቆር ግን #የአብይ አህመድ ፈረስ ለመሆን ግን ይሄን ያህል በደል መፈፀም አይጠበቅባችሁም ነበር። የአማራ ክልልን በግልፅም በስውርም እያፈረሱት ያሉት ከተላላኪ የአብይ አህመድ ፈረሶች ባሻገር የአማራ ልሂቃንም ጭምር መሆኑ ይታወቅ!! ፅሁፍን ላደረሱን ለንሥር እንግዳ እናመሰግናለን:: ድል ለአማራ ህዝብ!

Source: Link to the Post

Leave a Reply