መምህራኑ እና ሙሉ በሙሉ  እልባት ያላገኘው የደሞዝ ክፍያ እና መቆራረጥ ችግርበደቡብ  በማዕከላዊ ኢትዮጵያ  እንዲሁም  በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ያሉ መምህራን ደሞዝ እየተከፈልን አደለም እ…

መምህራኑ እና ሙሉ በሙሉ  እልባት ያላገኘው የደሞዝ ክፍያ እና መቆራረጥ ችግር

በደቡብ  በማዕከላዊ ኢትዮጵያ  እንዲሁም  በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ያሉ መምህራን ደሞዝ እየተከፈልን አደለም እንዲሁም   የውዝፍ ክፍያ ከ አመት በላይ አለመከፈሉን ለጣቢያችን ተናግረዋል

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በበኩል ዘላቂ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስቸግር ገልጿል።

ኢትዮ ኤፍ ኤምም  የችግሩን ስር መስደድ በመመልከት  ለኢትዮጵያ መምህራን ማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሐንስ በንቲ ፤ 

ለመምህራኑ ዘብ ከመቆም ባለፈስ እተሰሩ ያሉ ስራዎች ምንድናቸው በተለየም ከደሞዝ አለመከፈል እና መቆራረጥ ጋር ተያይዞ ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር  ዮሃንስ በንቲም ከትምህረት ሚኒሰትሩ ጋር ካደረግነው ውይይት ብዙ ችግሮች ተነስተው መልስ እንደተሠጠባቸው አንስተው፤ ይሁን እና  ችግሩ አሁንም በስፋት በአዳዲሶቹ ክልሎች እንዳለ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ ጨምረውም በተለይም የመምህራኑን ደሞዝ እና መሰል የክፍያ ጥያቄዎች ላይ  ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት ያሥቸግራል  ቢሆንም ግን ጥረቶች አለቆሙም በማለት ተናግረዋል

ለአብነትም በወላይታ ቸግሩን ብብዙ ፐርሰነት እንደቀረፉትም እንደማሳያ ጠቅሰውታል።

ጣቢያችንም በግጭት ውስጥ ባሉ ክልሎች ለአብነትም በአማራ ክልክ ያሉ መምህራንስ ያሉበትን መሰል ችግሮች ለመቅረፍ የእናንተ ማህበር ምን አይነት ጥያቄዎችን እያቀረበ ነው ሲል ጠይቋል።

ዶክተር ዮሃንስ በንቲም በአማራ ክልል የሚገኘው ማህበራቸው በክልል ያሉ አብዛኛው መምህራን ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው እንዳሳወቋቸው በማንሳት።

  የሰላሙ ሁኔታ መሰረታዊ ችግር ነው በዚህም ግጭት ባሉባቸው አካባቢዎች ያሉ መምህራኖች ክፍያዎች በአግባቡ እንዲደርሳቸው ከሚመለከተው አካል ጋር መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

በለአለም አሰፋ 

ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply