መምህርት እና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ በ50ሺ ብር ዋስትና ከእስር እንድትፈታ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ተፈታለች፤ መደበኛ ክርክሩም ለጥር 15 ተቀጥሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

መምህርት እና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ በ50ሺ ብር ዋስትና ከእስር እንድትፈታ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ተፈታለች፤ መደበኛ ክርክሩም ለጥር 15 ተቀጥሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ መምህርት እና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ታህሳስ 27/2015 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት ቀርባለች። ቀደም ሲል ታህሳስ 20/2015 በነበረው ቀጠሮ ዐቃቢ ህግ በ7 ቀናት ውስጥ ክስ መስርቶ እንዲቀርብ በሚል በተፈቀደለት መሰረት ታህሳስ 27/2015 ክስ መመስረቱን ለፍ/ቤት አስታውቋል። የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ መዘጋቱን ተከትሎ የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀጽ 14 በመተላለፍ ንቃት በተሰኘ በግል ሚዲያዋ ጥላቻን፣ አመጽንና ግጭትን ቀስቅሳለች ይላል። በተጨማሪም መከላከያን በብሄር በመከፋፈል ሀገርን ለማፍረስ በማሰብ የተፈጸመ ወንጀል ነው በሚል ሁለት ክስ የተመሰረተባት መሆኑን ነው ጠበቃ ሰለሞን ገዛኽኝ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የተናገረው። ሁለት ተከሳሾች መሆናቸው የታወቀው ዛሬ ነው ያለው ጠበቃ ሰለሞን ክሱም “በመስከረም ፀሀፊነት፣ በአምሓ ገደፋው ተራኪነት” ወንጀሉ በጋራ ተሳትፎ የተሰራ መሆኑን በመግለጽ የስራ ባልደረባዋ አምሓ ገደፋው በቁጥጥር ስር እንዲውል ትዕዛዝ እንዲጻፍ መደረጉ ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply