You are currently viewing መምህርት ፣ፀሐፊና ጋዜጠኛ ብርቱዋ መስከረም አበራ እንደከተበችው‼️ ***** የአማራ ህዝብ ላይ የሚወርደውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እና ከጭፍጨፋው ቀጥሎ ያለው የሁሉ ሰው ዝምታ(በተለይ የአማራው…

መምህርት ፣ፀሐፊና ጋዜጠኛ ብርቱዋ መስከረም አበራ እንደከተበችው‼️ ***** የአማራ ህዝብ ላይ የሚወርደውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እና ከጭፍጨፋው ቀጥሎ ያለው የሁሉ ሰው ዝምታ(በተለይ የአማራው…

መምህርት ፣ፀሐፊና ጋዜጠኛ ብርቱዋ መስከረም አበራ እንደከተበችው‼️ ***** የአማራ ህዝብ ላይ የሚወርደውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እና ከጭፍጨፋው ቀጥሎ ያለው የሁሉ ሰው ዝምታ(በተለይ የአማራው የራሱ ዝምታ በታሪክ የምናፍርበት ነው)፣የፌደራል/ክልል መንግስታት ምንም እንዳልተፈጠረ ባሸበረቀ ፓርክ ላይ የንጉስ ራት እየበሉ ስብሰባ መክፈት መዝጋት በኢትዮጵያ ላይ ብቻ የሚከናወን “አስደናቂ” ነገር ይመስለኛል። ይህን አስመልክቶ ስለሚያልቀው ንፁህ አማራ ነፍስ የምንሞግት ጥቂት ድምፆች ስማችን “ህዝብ ለህዝብ በሰላም እንዳይኖር የምናደርግ ፅንፈኛ ወይም አለቃሻ” ነው። የእኛ ስም እንዲህ ያለ የሆነው ድፍን አምስት አመት ሙሉ በሚያልቀው ህዝብ ቦታ ራሱን አስቀምጦ የሚሞግተው ሰው(የአማራ ልሂቅ) ቁጥር እጅግ በጣም አናሳ ስለሆነ ነው። በወለጋ፣ቤኒሻንጉል፣ጉራፈርዳ ስለሚታረደው፣ “አዲስ አበባ አትገባም” ተብሎ ከመኪና ወርዶ ሜዳ ላይ ለሚበተነው ፣ቄስ መነኩሴ ሳይል በጥፊም በጥይትም ስለሚመታውና ውርደት በላዩ ላይ ስለሆነው ህዝባችሁ የማትሞግቱት ለምንድን ነው? ስል በቀጥታ የምጠይቃቸው የአማራ ምሁራን፣ልሂቃን፣ባለሃብቶች የሚመልሱልኝ ተመሳሳይ መልስ “ልጆቻችንን እናሳድግበት” የሚል ነው!!!!! እዚህ ደመቀዝቃዛ መልስ ውስጥ ግዙፍ ራስ ወዳድነት አለ-“የእኔ ወላጅነት በልጆቻቸው ሁለት አይን ፊት ከሚያልቁ ወላጆች ወላጅነት በለጥ ያለ ነው፤ የልጆቼ ልጅነትም እንዲሁ እነዛ ጫካ ውስጥ ወላጅ አልባ ከሆኑ ህፃናት ልጆች በለጥ ያለ ልጅነት ነው” የሚል!!!! ለማንኛውም ዘመነም ልጆች አሉት!!!!! እኔም ልጆች አሉኝ!!!!! ሁሉም ልጅ እኩል ወላጆቹን ይፈልጋል ፣ሁሉም ወላጅ እኩል ልጆቹን ይወዳል። ልዩነቱ እንደ ዘመነ ያለው ወላጅነት የእርሱ ልጆች የሚፈልጉት የወላጅ እንክብካቤ፣ያገኙት የትምህርት እድል፣የሚለብሱት ንፁህ ልብስ እና የላመ የጣመ ምግብ ለሁሉም የሰው ልጆች የሚገባ ሰብዓዊ መብት መሆኑን የተረዳ ሻገር ያለ ወላጅነት መሆኑ ነው! እንዲህ ያለው ማንነት ነው ዘመነን በማይጨከነው በልጅ አስጨክኖ እስር ቤት ያስወረወረው! እነዚህ ልጆች ዛሬ የልጅ ልባቸው አባቱን ቢናፍቅም ነገ የሚኮሩበት ስራ ተሰርቶላቸዋል! #ምልክታችንን_ፍቱ

Source: Link to the Post

Leave a Reply