
መምህር መስከረም አበራ በችሎት ዛሬ የተናገረችው ተመዝግቧል።” አማራ ተነስቷል‼ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በእዚህ ችሎት በመቆሜ ለልጆቼ የምናገረው በኩራት ነው ነገ አያፍሩብኝም አሁን የአማራ ህዝብ ተነስቷል ከልጆቼ ተነጥዬ ይኽን መከራ የምከፍለው ከፀረ አማራ ሃይሎች ጋር አብሬ ባለመቆሜ ነው። ዛሬ የዋስትና ብይን ውሳኔ ጠብቄ ነበር ፍትህ ሳይሆን ውሳኔ ይሰጣል የሚል ጠብቄ ነበር ግን አልሆነም ዳኞች ለምን እንደተቀየሩ እንኳ የማወቅ መብት ነበረን እሱም አልሆነም። “..እኔ የታሰርኩት በፖለቲካ አመለካከቴ ነው ከ83 ጀምሮ ስልጣን የያዘ አማራ ጠል እስረኛ መሆኔን ነው የማውቀዉ ከዚህ ችሎት ምንም አይነት ፍትህ ላገኝ እንደማልች ቀድሜ አቀዋለሁ ዛሬ ይበልጥ አረጋግጫለሁ። ከ83 ጀምሮ በስልጣን የቆየ ፀረ አማራ ህዝባችን ጠበቃ እንዲኖረው አይፈልግም አማራን የሚጨፈጭፉ ሃይሎች ለሚሞተው ህዝብ የሚከራከር ጠበቃ እንዳይኖረው ይፈልጋሉ። የታሰረኩት አደባባይ ላይ እንድንቆም ባለመፈለጉ ነው ስለዚህ የፖለቲካ እስረኛ ነኝ። በእዚህ ችሎት በመቆሜ ለልጆቼ የምናገረው በኩራት ነው ነገ አያፍሩብኝም ። አሁን የአማራ ህዝብ ተነስቷል። ከልጆቼ ተነጥዬ ይኽን መከራ የምከፍለው ከፀረ አማራ ሃይሎች ጋር አብሬ ባለመቆሜ ነው። ከዚህ ክስ ፍትህ አልጠብቅም ለህዝቤ በከፈልኩት ዋጋ ክብር ይሰማኛል በፍጹም አልጸጸትም። ውጤቱ ምንም ይሁን እበረታለሁ አማራ ስለሆንኩ አልሰበርም። ሀምሌ 3/2015 ዓ,ም ታሪካዊ ንግግር ተመዝግቧል:: የዘገየ ፍትህ እንደ ተነፈገ ይቆጠራል (Justice Delayed Is Justice Denied )!! ለሐምሌ 12/2015 ዓ.ም ተቀጠሩ። በነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ የተከሰሱት የአማራ የህሊና እስረኞች በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ሶስተኛ ችሎት ተደርጓል ።ነገር ግን ስርዓቱ ሆን ብሎ የአማራ ምሁራን ፣ጋዜጠኞች ማህበራዊ አንቂዎች እና ሌሎች አማራ በመሆናቸውና ለአማራ ህዝብ ድምፅ በመሆናች በግፍ እሰር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ የፍትህ ስርዓቱን በማዛባት ፣ያለምንም በቂ ምክንያት ለመጪው ሐምሌ 12 /2015 ዓ.ም ተቀጥሯል ። በችሎቱ ላይ መምህርት ፣ጋዜጠኛ እና ፀሀፊ መስከረም አበራን ጨምሮ ሌሎች የህሊና እስረኞች ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ፣ጎበዜ ሲሳይ ወዘተ የታሰርነው “ለአማራ ህዝብ በመታገላችን የፓለቲካ እስረኞች መሆናቸውን ፤ የአንድ ብሔር የበላይነት በተያዘው ስርዓት ሰለባ መሆናቸውን እና በፍትህ ስርዓቱ እንደማያምኑበት ጭምር በልበ ሙሉነት አስደናቂና ታሪካዊ ንግግር አድርገዋል ። መረጃው የስንታየሁ ቸኮል ነው ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post