You are currently viewing መምህር ኃይሌ አወቀ መታፈኑ ተገለጸ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)    ግንቦት 10/2015 ዓ/ም       አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ከመምህርነት ሙያው ባሻገር በአማራ ማህበራዊ አንቂነት የብ…

መምህር ኃይሌ አወቀ መታፈኑ ተገለጸ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 10/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ከመምህርነት ሙያው ባሻገር በአማራ ማህበራዊ አንቂነት የብ…

መምህር ኃይሌ አወቀ መታፈኑ ተገለጸ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 10/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ከመምህርነት ሙያው ባሻገር በአማራ ማህበራዊ አንቂነት የብልጽግና አገዛዝን ገመና በማጋለጥ ለውጥ እንዲኖር በመታገል የሚታወቀው ኃይሌ አወቀ መታፈኑ ተገልጧል። ከስራ ውሎ ወደ ቤቱ ሲገባ ግንቦት 9/2015 ሲቪል በለበሱ አካላት መታፈኑ እና እስካሁን አድራሻው እንደማይታወቅ ተገልጧል። መምህር ኃይሌ አወቀ ከሰሞኑ የአገዛዙ ሰዎች በስሜ የእኔ ያልሆነ የቴሌግራም አካውንት በመክፈት ለመወንጀል እየሰሩ ነው፤ እያሳደዱኝም ነው ሲል ለአሚማ ገልጾ ነበር።

Source: Link to the Post

Leave a Reply