መምሕራን ለበጎ ሥራ እየተጠሩ ነው

https://gdb.voanews.com/E2E32B68-D1E3-43A6-963D-09BE3AACD93F_cx0_cy0_cw93_w800_h450.jpg

ኢትዮጵያ በጡረታ ላይ ያሉና በሌሎች ሥራዎች ላይ የተሰማሩ መምሕራንን ለበጎ ፈቃድ የማስተማር ሥራ እየጠራች ነው። መምህራኑ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሲባል ቁጥራቸው በሚጨምረው የመማሪያ ክፍሎች ምክንያት የሚፈጠረውን ጫና ለመቀነስ እንደሚያግዙ ተነግሯል።

የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያም “እኔም አስተምራለሁ” በሚል መሪ ቃል ይፋ የተደረገውን ንቅናቄ በመቀላቀል ዛሬ በዳግማዊ ምኒሊክ ሁለተኛ ደረጃትምሕርት ቤት ተገኝተው ማስተማር ጀምረዋል።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ደግሞ ሌሎች በጎ ፈቃደኛችም ንቅናቄውን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ለ45 ቀናት የሚሰጠው የ8ኛ እና የ12 ክፍል የገጽ ለገጽ የማካካሻ ትምሕርት ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply