በትግራይ ክልል መንግስት ከወሰደው የህግ ማስከበር ርምጃ በኋላ ከውጭ መገናኛ ብዙን ጀምሮ በማኅበራዊ ሚዲያና ከተለያዩ አካላት የሚሰሙ ጉዳዮች ማብራሪያ ማስተባበያና ማስተካከያ ሳይሰጥባቸው በንቀት ዝም ብሎ መመልከትተገቢ ካለመሆኑም በላይ የህዝብን ልብ የሚያሻክር አብሮ ለመኖርም የማይጠቅም በመሆኑ በበርቱ ሊታሰብበት የሚገባ ተግባር ነው፡፡
ተመሪው ሕዝብ ስለመሪው አቅጣጫና ግብ በበቂ ሁኔታ ካልተረዳ ትክክለኛ ተመሪ ሊሆን አይችልም፡፡ በትክክል ካልተመራ ደግሞ መበተኑ አይቀርም፡፡ ስለዚህ በተለይ መረጃን ለሕዝብ በአግባቡ ለማድረስ የሚሠራ አንድ ጠንካራ ቡድን ወይም ተቋም ሊኖር ይገባል የሳምንቱ አብይ ጉዳይ::
አዘጋጅ:ሰላም ሰይፉ
ቀን 30/04/2013
ዐብይ ጉዳይ
Source: Link to the Post