መረጃ‼️ በኦሮሚያ ክልል ያዮ ከተማ በቅርብ ርቀት በሚገኘው ወረቦ በሚባል ሰፈር ንፁሀን የአማራ ተወላጆች ላይ በኦሮሚያ ነፃነት ሰራዊት ጥቃት መፈፀሙ ተሰማ! በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ነፃ…

መረጃ‼️ በኦሮሚያ ክልል ያዮ ከተማ በቅርብ ርቀት በሚገኘው ወረቦ በሚባል ሰፈር ንፁሀን የአማራ ተወላጆች ላይ በኦሮሚያ ነፃነት ሰራዊት ጥቃት መፈፀሙ ተሰማ! በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኢሉባቡር ዶረኒ ወረዳ ወረቦ ቀበሌ ገብቶ ጥምባ በምትባል አካባቢ ተኩስ ከፍቶ አምሽቷል። ቁጥራቸው ከ1000 በላይ የሚሆኑ ታጣቂዎች ከዳሪሙና አልጌ ተነስተው ወደ ወረቦ መግባታቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። በዚሁ አካባቢ መከላከያው ሰራዊት ሰሞኑን መውጣቱን ተከትሎ ታጣቂዎች ንፁሃንን ሊጨፈጭፉ ስለመጡ የሚመለከተው የፀጥታ አካል እንዲደርስልን ሲሉ ተማፅነዋል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply