#መረጃ በመንግስት የሚታገዘው የሽብር ቡድን ኦነግ መጠነ ሰፊ ጥቃት በሸዋሮቢት ዙሪያ እየፈጸመ መሆኑ ተነገረ! ባህርዳር:- ሚያዚያ 10/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚ…

#መረጃ በመንግስት የሚታገዘው የሽብር ቡድን ኦነግ መጠነ ሰፊ ጥቃት በሸዋሮቢት ዙሪያ እየፈጸመ መሆኑ ተነገረ! ባህርዳር:- ሚያዚያ 10/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ የፌደራል ሰራዊት ውጥረቱን ማረጋጋት አልፈለገም የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ትህዛዝ አልተሰጠኝም ማለቱ ችግሩን እንዳያባብሰው ተፈርቷል። ትላንት ማምሻዉን በሰሜን ሸዋ በሞላሌ ነጌሶ ድንገታዊ ጦርነት የከፈተዉ የስርዓቱ ክንፍ ሽብርተኛዉ የኦነግ ሰራዊት በርካታ ሃይል ከኬሚሴና ሰንበቴ በማሰባሰብ በነጌሶ የአማራ ቤቶችን እያወደመ በማምሸት በጀዉሃ እንዲሁም ዛሬ በሸዋሮቢት ቀበሌ 5 ላይ ጥቃት እያደረሰ መሆኑ ታውቋል። በመደበኛ ሰራዊት ደረጃ ትጥቅ የያዘ የሽብር ቡድኑ ኦነግ የጦርነት ትንኮሳዉን ለመመከት የአካባቢዉ ሚኒሻና ፋኖ እየተከላከለ ሲሆን ችግሩን ለማስቆም የተጠየቀው የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ከበላይ አመራር ትህዛዝ አልተሰጠኝም ማለቱ ተሰምቷል። በሽብር ሃይሉ የሚደርስ ውድመት አካባቢዉን ወደከፋ ቀውስ እንዳይከተው ተፈርቷል። በአሁን ሰዓት ሸዋሮቢት ዙሪያ ከትላንት ጀምሮ ያልቀዘቀዘ ውግያ ያለ ሲሆን በኦነግ ሃይል መጠነ ሰፊ ጥቃት በነዋሪው ላይ እየተፈጸመ እንዳለ ታውቋል። #ስንታየሁ ቸኮል ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply