#መረጃ በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳአያና ወረዳ ኢጀሬ በተባለ ቀበሌ ከአንገር ጉትን ከተማ ከመንደር 12 ቀበሌ ኦነግ ሸኔን ለመደምሰስ ዝመቱ ተብለው የሔዱትን የአማራ ተወላጂ የሚኒሻ አባሎች በ…

#መረጃ በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳአያና ወረዳ ኢጀሬ በተባለ ቀበሌ ከአንገር ጉትን ከተማ ከመንደር 12 ቀበሌ ኦነግ ሸኔን ለመደምሰስ ዝመቱ ተብለው የሔዱትን የአማራ ተወላጂ የሚኒሻ አባሎች በወረዳው የፀጥታ ዘርፍ ሐላፊ በረሐብ እየተሰቃዩ እንደሆነ ተገለፀ! ባህርዳር:- ሚያዚያ 12/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ከአንገር ጉትን መንደር 12 የተወሰዱ አማራ ምኒሻዎች ከጊዳ አያና ወረዳ እስከ 40-60 ኪሎሜትር እርቀት በሚገኝ አካባቢ 10 የሚሆኑ ምኒሻወች በክልሉ መንግስት አካባቢውን እንዲጠብቁ በማለት ተወስደው እልም ያለ ጫካ ውስጥ በማስቀመጥ ስንቅና ለጥበቃ የሚሆን የተሟላ መሣሪያም አልተሰጣቸው ሲሉ ምንጫችን ገልፀዋል ። በአስቸጋሪ ውስጥ እንደሚገኙና ወደ ጉትን ሰፈራቸው እንዳይመለሱ ከጀርባቸው የኦሮሚያ ልዩሃይልና የአካባቢው ሚሊሻ በአይነ ቁራኛ እየተከታተሏቸው እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን ከፊት ለፊት ደግሞ አራጁ ሸኔ አፍጥጦ እየጠበቃቸው መሆኑ ችግሩ በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ ሆኖባቸዋል ብለዋል። በአካባቢው የነበረው መከላከያ ለቆ ሂዷል፣ ሸኔና የሸኔው ደጋፊ የኦሮሚያ ሚሊሻ ከመካከል አድርገው እያሰቃዩአቸው ስለሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ድምፅ እንዲሆናቸው የአካባቢው ኑዋሪ የሆኑ ምንጫችን ተናግረዋል ። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply