# መረጃ #በኦሮሞ ብልፅግና የተጨፈለቀው የአዲስ አበባ ነዋሪ ለቅሶ! በአዲስ አበባ ለቡ ገብርኤል በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የታገዘ ህገወጥ የቤት ፈረሳ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ !! ታሕሳስ 25 ቀ…

# መረጃ #በኦሮሞ ብልፅግና የተጨፈለቀው የአዲስ አበባ ነዋሪ ለቅሶ! በአዲስ አበባ ለቡ ገብርኤል በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የታገዘ ህገወጥ የቤት ፈረሳ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ !! ታሕሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ “የአዲስ አበባ ሕዝብ የመጨረሻ እጣ ፈንታዉ ይኸው ነው። ለቡ ባቡር ጣቢያ መጤ ውጡ ተብለው የሚፈናቀሉ የአማራ ወገኖች የለቅሶ ድምፅ ለሚመለከተው ሁሉ በማድረስ ሼር በማድረግ እናሳውቅ። በጥይት የተመቱ ሰዎች ቁጥራቸው አምስት መድረሱ ተሰምቷል። ከኦሮሚያ ዉጭ የሆኑትን ተወላጆች ለማባረር ዛሬ ሌሊት 11:00 ሰዓት ጀምሮ ለቡ ገብርኤል አካባቢ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የታገዘ ህገወጥ የቤት ፈረሳ እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ። እንቁ ገብርኤል በተለምዶ ለቡ ባቡር ጣቢያ አካባቢ ተብሎ በሚጠራው 20 ዓመት እና ከዚያ በላይ የኖሩበትን ቤት መጤ በማለት ከኦሮሚያ ዉጭ የሆኑትን ተወላጆች ቤት በማፍረስ ለማባረር ዛሬ ሌሊት 11:00 ሰዓት ጀምሮ የኦሮሚያ መንግስት አፍራሽ ኃይል አቋቁሞ እያፈረሰ መሆኑን ከቦታው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ይህን ሂደት አስቀድመን ለማስቆም ለፌደራል መንግስት ለማመልከት ወደ ቤተ-መንግስት ገብተን የተሰጠን ምላሽ ከክልሉ መንግስት ጋር ጨርሱ የሚል መልስ ነው። የክልሉ መንግስት ደግሞ አንድም መጤ እንዳይኖር ብሎ አቶ ሽመልስ አስተላልፏል በሚል ምንም ተቀባይነት አተናል። አልፎ ተርፎ ወደ ሚዲያ ኢቢሲ የብዙኸን መገናኛ ብናናግር የደረሰለን የለም። ማፍረስ የጀመሩት ሌሊት 11:00 ሰዓት ነዉ። ስለዚህ እባካችሁ ድረሱልን ሲሉ ተማፅነዋል። ዘገባው የፅናት ሚዲያ ነው። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply