
# መረጃ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከልዩ ጽ/ቤታቸው ያሰናበቱት ደብዳቤ ተመልከቱ‼ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ይህ ሰው (ሰረቀ) በቅዱስነታቸው ላይ ቂም ስለያዘ የሚመሯትን ቤተ ክርስቲያን ለመክፈል ይኽን ያኽል ተጉዟል። ከዚህ በላይ ሰይጣናዊ ሥራ የለም። ይኽም ቀድሞ ተነግሮበታል። ግለሰቡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ለጵጵስና ብዙ ደጅ ጠንቷል። እርሳቸው ግን ትንቢታዊ በኾነ ቃል “ለአንተ ጵጵስና ሰጥቼ ቤተ ክርስቲያኔን በዘመኔ አልከፍልም” ብለው ተስፋ አስቆረጡት። በደብዳቤው ላይ ሦስት ወራት ባልሞሉ ጊዜያት ውስጥ ባሳዩት የችኩልነትና አለመረጋጋት ባሕርይ በአደራ የታጣለብዎትን የሥራ ኃላፊነት በአግባቡ አለመወጣታቸው ተገልጧል። ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል ቆርጠው እየተንቀሳቀሱ ያሉት እንደነዚህ ያሉትን መንፈሳዊነት የጎደላቸውን የህወሓት ፖለቲከኛን ለማንገስ መሆኑ ግልጽ ነው። ደብዳቤው የሚከተለው ነው:_ እንደሚታወቀው ሁሉ ከሐምሌ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ የቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጸሐፊ ሆነው ይሠሩ ዘንድ በቁጥር ል/ጽ/474/420/2008 በተጻፈ ደብዳቤ መመደብዎ ይታወቃል። ይሁንና ሦስት ወራት ባልሞሉ ጊዜያት ውስጥ ባሳዩት የችኩልነትና አለመረጋጋት ባሕርይ በአደራ የታጣለብዎትን የሥራ ኃላፊነት በአግባቡ አለመወጣትዎ፣ የበላይ ኃላፊዎችዎን ትእዛዝ አለማክበርዎና አለመቀበልዎ፣ በጠቅላላ የሚያሳዩት መንፈስ ከሥራው ጠባይ ጋር አብሮ የማይሔድና የማይጣጣም ሆኖ በመገኘቱ በሥራው ላይ ችግር ተፈጥሯል፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ የጸሐፊነት ሥራ የተነሡ መሆንዎን እየገለፅን የጽሕፈት ቤቱን ቁልፍና ንብረት ለሊቴ አሰፋ ሥዩም አስረክበው ደመወዝዎን እንደያዙ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉ እናስታውቃለን ፡፡ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post