You are currently viewing #መረጃ! ኤርሚያስ መኩሪያን ጨምሮ 20 አማራዎች በመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ መምሪያ ታፍነው እንደሚገኙ ታወቀ! ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ኤርሚያስ መኩሪያ ግንቦት 4…

#መረጃ! ኤርሚያስ መኩሪያን ጨምሮ 20 አማራዎች በመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ መምሪያ ታፍነው እንደሚገኙ ታወቀ! ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ኤርሚያስ መኩሪያ ግንቦት 4…

#መረጃ! ኤርሚያስ መኩሪያን ጨምሮ 20 አማራዎች በመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ መምሪያ ታፍነው እንደሚገኙ ታወቀ! ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ኤርሚያስ መኩሪያ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከቤቱ በመውጣት ወደ መርካቶ እየተጓዘ በነበረበት ወቅት የመከላከያ ኮማንዶዎችና የደህንነት አባላት አፈና እንደተፈፀመበት ይታወቃል። ከዚህ ዕለት ጀምሮ ቤተሰቦች በሁሉም እስር ቤቶች ቢያንኳኩም የት እንዳለ ለማወቅ አልተቻለም ነበር። ከወታደራዊ ምንጮቻችን እንዳረጋገጥነው፤ ኤርሚያስ መኩሪያን ጨምሮ 20 አማራዎች ሳር ቤት በሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል። አፈናውን የፈፀሙት የመከላከያ ሰራዊት ኮማንዶች እንደሆኑ የሚታወቅ ሲሆን እንደ ወታደራዊ ምንጮቻችን ከሆነ የሕዝቡ የመጠየቅ ስሜት በማየት ተዋቸው እንጂ ግድያ ሊፈፀምባቸው እንደነበር ታውቋል። በብርሃኑ ጁላ የሚመራው የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ መምሪያዎች የንጹሃን ዜጎች ማጎሪያ ከሆነ መሰነባበቱን የወታደራዊ መረጃ ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል። ምንጭ:- Mereja Tv “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply