መረጃ!!! የባልደራሱ ኢንጂነር መለሰ ደባስ በድጋሜ ፍ/ቤት ቀረበ! ጥር 4 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የጉለሌ ክ/ከተማ ስራ አስፈፃሚ የ2…

መረጃ!!! የባልደራሱ ኢንጂነር መለሰ ደባስ በድጋሜ ፍ/ቤት ቀረበ! ጥር 4 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የጉለሌ ክ/ከተማ ስራ አስፈፃሚ የ2013 ዓ.ም አዲስ አበባን በመወከል ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረዉ ኢንጂነር መለሰ ደባስ በ2/5/2015 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት በዋለዉ ችሎት በ20 ሺ ብር ዋስትና እንዲፈታ ዉሳኔ ቢሰጥም መርማሪ ፓሊስ ከህግ ዉጭ በማፈን ከሁለት ቀናት በኋላ ዛሬ በ4/5/2015 ዓ.ም በጠቅላይ ፍ/ቤት ቀረበ። ፍ/ቤቱ መርማሪ ፓሊስ ይግባኝ የጠየክበትን ወንጀሉን በዝርዝር ለችሎቱ አስረዳ በማለት የጀመር ሲሆን፤ #አዳነች አቤቤን እና አብይ አህመድን በማህበራዊ ሚዲያ ዳቦ አሲይዞ ለቋል :: መንግስትንም አብዝቶ ይተቻል:: #በየት/ቤቶች በመቀሳቀስ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥሯል የሚል ክስ ፖሊስ ይዞ ቀርቧል። #በዚህ ጉዳይ ላይ ኢንጂነር መለሰ ደባስ በችሎቱ ሰፊ ክርክር በማድርግ የሚከተሉትን መሰረታዊ ነጥቦች አንስቷል ። # የባልደራስ የክ/ከተማ ስራ አስፈፃሚ እና አዲስ አበባን ወክሎ የ2013 ዓ.ም ዕጩ ተወዳዳሪ መሆኑን በመግለፅ በየት/ቤቶች ተንቀሳቅሰህ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥርሃል፤ ለተባለዉ መልስ ሲሰጥ ስራው የግል የዉጭ ካምፓኒ ዳሬክተር እንደሆነ በመግለፅ ፤ በስሩም ብዛት ያላቸዉ ሰራተኞችን በኃላፊነት እንደሚያስተዳድር ተናግሯል። በየቦታዉ ዞሬ ሁከትና ብጥብጥ ልፈጥር ቀርቶ የስራ እረፍት የለኝም ፤ ለዚህም ከመስሪያ ቤት ስራ ቦታ መገኘቴን የሚገልፅ ሰነድ አቀረባለሁ ሲል መልስ ሰጧል። የእሱ መታሰር በመስሪያ ቤቱ እንደ ግል፤ እንዲሁም የቤተሰብ አስተዳዳሪም ነኝ ብሏል። እንደ አገር ደግሞ ብዙ ሰራተኞችን አቅፎ የያዘዉ ካምፓኒ ስለሆነ ጉዳት አለዉ ሲል ለችሎቱ አስረድቷል። #መርማሪ ፓሊስ በየት/ቤቶች እየተንቀሳቀሰ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥሯል ላለዉ የት ቦታ? መቼ? ሰዓት? ዝርዝር መረጃ ባለቀረበበት ሁኔታ ልታሰር አይገባም ብሏል። #ከፍ/ቤት ትዕዛዝ ዉጭ በተያዝኩበት ጊዜ ብዛት ያላቸዉ በቁጥር አምስት (5) ደህንነቶች ባሉበት በፀጥታ አካላት ከባድ ድብደባ ተፈፅሞብኛል ሲል ጨምሮ ተናግሯል ። #ከፍ/ቤት ትዕዛዝ ዉጭ በቤተሰቦቼ መኖሪያ ቤት ፍተሻ በማድረግ ሞባይል፣ላፕቶፕ እና የባልደራስ ፓርቲ ፕሮሸሮችና የግል ሰነዶች ተወስደዉብኛል ብሏል። #በማህበራዊ ሚዲያም ቢሆን ሃሳቤን በነፃነት የመግለፅ መብት ሊኖረኝ ይገባል እንጂ መርማሪ ፓሊስ እንደ አገር ሊያገልግል እንጂ እንደ ግለሰብ አዳነች አቤቤ ና ጠ/ሚ አብይ አህመድን ተችተሃል በማለት ልታሰር አይገባም በማለት በ2/5/2015 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት በዋለዉ ችሎት በዋስትና ዉሳኔ የተሰጠዉን ትዕዛዝ እንዲከበርለት እና ጉዳዩን በዉጭ ሁኖ እንዲከታተል ለጠቅላይ ፍ/ቤቱ ዉሳኔ እንዲሰጥለት ሰፊ የሆነ ክርክር የግፍ እስረኛዉ በችሎቱ ፊት አድርጓል ። መርማሪ ፓሊስ የተጠርጣሪ ኢንጂነር መለሰ ደባስን የክርክር ነጥቦችን ከሰማ በኋላ፤ # ተጠርጣሪ በዋስ የሚፈታ ከሆነ ምስክሮቼን ጫና ይፈጥርባቸዋል ። በተጨማሪም በዋስ ከወጣ በቀጠሮ ቀን ላይገኝ ይችላል የሚል ግምት አለኝ በማለት የተለመደዉን ምክንያት አቅርቧል ። ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ካዳመጠ በኋላ መርማሪ ፓሊስ አለኝ የሚለዉን መረጃ ይዞ እንዲቀርብ ለጥር 8/5/2015 ዓ. ም ስድስት ኪሎ በሚገኘዉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል። መረጃው የአስካል ደምሌ ነው ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply