# መረጃ :- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚኒሽን በአማራ ፖሊሶች ልዩ ክትትል እንዲጀመር ታዘዘ ! አሻራ ከሰ.አሜሪካ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚኒሽን ለፋኖ ይቀርባሉ በተባሉ የአማራ ፖሊሶች ላይ…

# መረጃ :- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚኒሽን በአማራ ፖሊሶች ልዩ ክትትል እንዲጀመር ታዘዘ ! አሻራ ከሰ.አሜሪካ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚኒሽን ለፋኖ ይቀርባሉ በተባሉ የአማራ ፖሊሶች ላይ ልዩ ክትትል እንዲጀመር ለተመረጡ አመራር መኮንኖች መመሪያ ተሰጥቷል ተባለ። በግምገማ አስቸጋሪ የተባሉ አባላት መሳሪያቸው እንዲነጠቁ ተወስኗል ከጽንፈኛዉ “ፋኖ” ጋር በመሆን ድጋፍና ትብብር የሚያደርጉ የፖሊስ አባላት የእጅ ስልካቸው ተቀምቶ ፎቶ እና የፌስቡክ አካውንት እንዲታይ እንዲሁም በተለየ ሁኔታ ከፖሊስ ሰራዊት ዲስፕሊን ውጪ ወገንተኝነት የሚታይባቸው አባላት በአስቸኳይ እንዲታሰሩ ታዟል። የሚሉት የመረጃ ምንጫችን በቁጥጥር ስር የሚውሉት የፖሊስ አባላት ወደ ማሰልጠኛ እንዲላኩ አቅጣጫ መቀመጡ ከውስጥ ተሰምቷል። ይህ በአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት የተጀመረው አፈሳና ማንነትን መሰረት ያደረገ ዘመቻ እንደ ሕዝብ የታቀደ ነው በማለት በሁሉም መምሪያ ጣቢያዎች ተመሳሳይ አቅጣጫ እንደሚከተሉ በመገንዘብ ከወዲሁ በስነ ልቦና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ለአባላቱ መልዕክታቸውን አሳስበዋል። @ ስንታየሁ ቸኮል

Source: Link to the Post

Leave a Reply