
መረጃ ጎንደር አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ ዛሬ በቀን 22/09/2014 ዓ.ም የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፋኖ አማራ ምንሊክ ብርጌድ ዋና አዛዥ ሻለቃ አንተነህ ድረስ ላይ በዋለው ችሎት ተከሳሽ ምንም አይነት ክስ ከየትኛውም ወገን እንዳልቀረበበት የገለፀ ቢሆንም በዞኑ የሰላምና ደህንነት መምሪያ በኩል ግን ክስ እንዳለበት ለከፍተኛው ፍርድ ቤት እንዳቀረቡና አሁንም ሌሎች የሀሰትና የፈጠራ ክሶችን ለማቅረብ እንደትዘጋጁ ለማወቅ ችለናል ብሏል ፡፡ ይህንን ተከትሎም ችሎቱ በነገው እለት ማለትም በቀን 23/09/2014 ዓ.ም በድጋሜ እንዲታይ መደረጉን ከታማኝ ምንጮች አረጋግጠናል
Source: Link to the Post