You are currently viewing “መሪዎችን እያዋካቡ ማስመረር የሃገራችንን ፖለቲካ የተጣባው ጉዳይ ነው። ይህ የመንግስት አካሄድ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። መንግስት ከዚህ ድርጊቱ ሊታቀብ ይገባል።” ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞ…

“መሪዎችን እያዋካቡ ማስመረር የሃገራችንን ፖለቲካ የተጣባው ጉዳይ ነው። ይህ የመንግስት አካሄድ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። መንግስት ከዚህ ድርጊቱ ሊታቀብ ይገባል።” ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞ…

“መሪዎችን እያዋካቡ ማስመረር የሃገራችንን ፖለቲካ የተጣባው ጉዳይ ነው። ይህ የመንግስት አካሄድ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። መንግስት ከዚህ ድርጊቱ ሊታቀብ ይገባል።” ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ነሃሴ 9 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ባልደራስ በወቅታዊ ሀገራዊ እና ድርጅታዊ ጉዳይ የሰጠው ሙሉ መግለጫ:_ የትግላችን ባቡር የፍጥነት ማርሹን ቀይሮ ወደፊት ይራመዳል ! የባልደራስ ድጋፍ በሰሜን አሜሪካ መግለጫ ባልደራስ ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት ከመቀየሩ በፊት የሃገራችን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ላይ የተነሳውን ጸረ እኩልነት ጥያቄዎች አንግቦ ሲታገል እንደነበር ይታወቃል። በአንድ እናት ልጆች መካከል የልዩ ጥቅም እሳቤ አይኖርም፣ ልዩ ጥቅም የሚባል አስተሳሰብ ከሃገራችን፣ ከምድራችን የቃል ኪዳን ሰነድ ላይ ጨርሶ መፋቅ አለበት፣ አዲስ አበባ ብሎም ኢትዮጵያ ልጆቿን ሁሉ እኩል አይታ የምትተዳደርበት ስርዓት ይፈጠር የሚለውን ጉዳይን አንስቶ ባልደራስ ትግሉን ሲያቀጣጥል በዚህ ሃሳቡ የሚሊዮኖችን ልብ መማረክ ችሏል። ባልደራስ የዚህን የመዋቅር ጥያቄና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ግዝፈት ከተረዳ በሁዋላ መላ የንቅናቄውን አባላት አማከረ። በዚህ ጊዜ በሃገር ውስጥ ያሉት አባላቱና ውጪ ሃገር ያሉት ደጋፊዎች በአንድ ድምጽ ባልደራስ ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት እንዲቀየርና የፖለቲካ ስልጣን ይዞ እኩልነትና መልካም ኣስተዳደር ለማስፈን ለሃገራችን ሳይታክት ሊሰራ ይገባል ብሎ መወሰኑን ተከትሎ ባልደራስ ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት ተቀየረ። ታዲያ ባልደራስ ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት ሲቀየር መሬት ላይ ያለውን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ነባራዊ ሁኔታ ካጠና በሁዋላ ባለ ሁለት ክንፍ አድርጎ ራሱን አደራጀ። ይህም ማለት በአንድ በኩል የፖሊሲ ጉዳዮችንና የመዋቅር ጉዳዮችን እያጠና ፖሊሲ የሚቀርጽበትን ኣንድ ክንፍ ፈጠረና በሌላ በኩል በየጊዜው የሚደርሰውን የህዝብ እንባ የሚጠብቅ፣ ህዝቡ ሲገፉ ደርሶ የሚጠይቅ፣ ለተገፉ ጠበቃ የመሆን የአክቲቪዝም ስራ በፈቃደኝነት ተረክቦ እነሆ በሁለት ክንፍ መብረር ጀመረ። በዚህ ጊዜ ድሆች ያለ ኣግባብ ቤታቸው ሲፈርስ ደርሶ የሚያጋልጥ፣ ታግሎ የሚያታገል ትንታግ የድሆች መከታ ሆኖ ወጣ። ባለ ሃብቱ የሚደርስበትን መድልዎና አንግልት ለማጋለጥ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ባልደራስ መከታ ሆኖ ታየ። የሀገራችንን የፖለቲካ ሰልፎች በጥንቃቄ በመተንተን የተረኝነት ኣስተሳሰብ እንዳለ፣ ተረኝነት ምልክቶቹ እየፈኩ እንደመጡ ገና በጠዋቱ በጀግንነትና በሃቀኝነት ያጋለጠ ብቸኛ ፓርቲ ሆነ። ባልደራስ ገና በማለዳ የአዲስ አበባ ህዝብ እንዲነቃ ሲታገል የቆየባቸው የተረኝነት ምልክቶች አድገው አድገው ዛሬ ላይ የተረኝነቱ ልክ የት እንደደረሰ ሁሉም የሚያወቀውና የሚመዝነው ጉዳይ ነው። ታዲያ ባልደራስ ይህንን ለተገፉ ጠበቃ ሆኖ የመቆሙን ስራ ሲያከናውን በእውነት ተመችቶት አልነበረም። ከዚህም ከዚያም ፍላጻዎች ይወረወሩበታል። በመንግስት በኩል እስራትና እንግልት የቀን ተቀን ፈተና ነው፣ በአድር ባይ ፖለቲከኞች ዘንድ ደግሞ የተቃውሞ ፍላጻዎች ይተኮሱበት ነበር። የፖለቲካ ፓርቲ ሆናችሁ ለምን ኣክቲቪስት ትሆናላችሁ? የፖለቲካ ፓርቲ ስራው ፖሊሲ መቅረጽ ብቻ ነው። የሚል ትችት በየቀኑ ይቀርቡበት ነበር። ነገር ግን የተጠናከረ የፍትህ አካላትና መልካም አስተዳደር በሌለበት አገር፣ የሰባዊ መብት ተቋማት ነጻነታቸው በጎደለበት ሃገር፣ ህዝባችን በፍትህ አጦት ሲሰቃይ፣ የለም እኛ ፖሊሲ ቀርጸን በምርጫ ኣሸንፈን ስልጣን ስንይዝ ብቻ ነው የምንረዳህ ብሎ ከተገፉው ህዝብ ዘንድ ባልደራስ ፊቱን ለማዞር ከቶውንም አንጀቱ ኣልቻለም። ፓርቲው ሰው ሰው ይሸት ዘንድ ያስፈልጋልና ከተገፉ ዘንድ ቆሞ ሲያለቅሱ ኣልቅሶ፣ ብሶት ኣዳምጦ፣የሚችለውን ድጋፍ ሁሉ ማሳየት ጥበብ ሆኖ ታይቶናል። ይህ የባልደራስ እምነት በርግጥ ወቅታዊና ተገቢም ነው ብለን እናምናለን። ባልደራስ በሃገራችን ውስጥ ብቸኛ ቀኝ ዘመም ፓርቲ ሲሆን መንግስት ቅርሶችን ሲያፈርስ ሃይ ማለትና ድምጽን ማሰማት የቀን ተቀን ስራው ነው። ሃገራችን ኢትዮጵያ ታላቅ አገር ናት ስንል ህያው ምስክሮቹዋ የታሪክ ኣሻራዎቻችን ናቸው። የቀደመወን ትውልድ ጥበብ መጠበቅ የታሪክ ተለጣጣቂነት መፍጠርና ወደ ፊት ለተሻለ ህይወት መዘርጋት ለሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ነው። ዛሬ ኣደጉ፣ በለጸጉ የምንላቸው ሃገራት ያለፈውንና የዚህን ትውልድ ጥበቦች እያጋቡ ነው እድገታቸው የተሳለጠው። በተለይ ኢትዮጵያ ደግሞ ተጨባጭ የሆኑና ያልሆኑ ቁሳዊና መንፈሳዊ ባህሎቿን መጠበቅና መንከባከብ አለባት። አገጭ እጓ ሳይል የረጋ ሃገረ መንግስት መስርተን የምንኖረው ተለጣጣቂነትን ስናሳልጥ ነው፣ ከተረኝነት አዙሪት ስንወጣ ነው። ባልደራስ ለኣዲስ ኣበባ ህዝብ መከታ ሆኖ የቆየ ፓርቲ ሲሆን እነሆ ዛሬ ሃገራዊ ፓርቲ በመሆን ለኢትዮጵያ መድህን ለመሆን ደፋ ቀና ይላል። የዋና ከተማችን መዋቅራዊ ችግሮች የሚፈቱት የሃገሪቱ ኣጠቃላይ የመዋቅር ለውጥ ሲመጣ አንደሆነ ያምናል። ይሁን እንጂ በዚህ እንቅስቃሴው ወቅት የድርጅቱን አመራር አቶ ስንታየሁ ቸኮልን ጨምሮ የባልደራስ አባላት በየጊዜው ሲታሰሩ ሲፈቱ ነው የምናየው። መንግስት ይህንን ሃቀኛ የሆነ ፓርቲ ለማዳከም የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። በየጊዜው የፓርቲውን አመራሮች ማሰር ማንገላታት፣ ማስፈራራት፣ ተጽእኖ መፍጠር በየእለቱ በባልደራስ ላይ የሚያርፉ የመንግስት ዱላዎች ናቸው። የባልደራስ አመራር በዚህ ሁሉ ተጽእኖ ውስጥ ተቋቁሞ በሃገርና በውጭ ሃገር ተጠናክሮ ትግሉን ቀጥሉኣል። በእኛ እምነት የባልደራስ አመራርና የፓርቲው ኣባላት ለምንወዳት ሃገራችን የሚከፈለው ዋጋ ሊመጣ ካለውና ከምናልመው የሃገራችን በጎነት ኣንጻር ሲታይ አንደ ኢምንት ነው ብለው ማመናቸው ድርጅቱ የሃገር ተስፋ እንዲሆን አድርጎታል። በዚህ የፓርቲው አቋም እኛ የሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ሰጪ አባላትና አመራሮች ያለንን አድናቆት እንገልጻለን። ዛሬ ላይ የባልደራስ ፕሬዝደንት ኣቶ አስክንድር ነጋ በደረሰባቸው ከባድ ተጽእኖ በኣባልነትም ሆነ በኣመራርነት መቀጠል አልቻልኩም ብለው ፓርቲውን ለቀዋል። መሪዎችን እያዋካቡ ማስመረር የሃገራችንን ፖለቲካ የተጣባው ጉዳይ ነው። ይህ የመንግስት አካሄድ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። መንግስት ከዚህ ድርጊቱ ሊታቀብ ይገባል። አቶ እስክንድር ተማረው ባልደራስን ቢለቁም ፓርቲው እንደ ፓርቲ በህዝባችን ልብ ውስጥ የገባ የድሆች ጠበቃ ትግሉን ከመቼውም ጊዜ በላይ ኣጠናክሮ አንደሚቀጥል ሁሉም ሊያውቅ ይገባል። በትግላችን ውስጥ የአመራር ሽግሽግ ቢኖር፣ የኣባላት ለውጥ ቢኖር፣ መውጣት መውረድ ቢኖር፣ የትግሉ ባቡር በሃዲዱ ላይ ለሰከንድ አይቆምም። የህዝብ ብሶት የፈጠረው ባልደራስ ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ በእልህና በቁጭት ኣመራሩና ኣባላቱ በአጭር ታጥቀው ትግሉን ሊመሩ ሊያራምዱ ቃል ገብተዋል። ባልደራስ ያነገበው አላማ ከሲቪክ ንቅናቄነት ገፍቶ ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት የቀየረው ግዙፍ፣ ቅዱስና ሃያል ጉዳይ በመሆኑ በየጊዜው ሃይላችንን እያደሰን ወደ ፊት አንድንዘረጋ ያደርገናል። ባልደራስ አስካሁን የአዲስ ኣበባ ፓርቲ ቢሆንም በኣዲስ ኣበባ ኣካባቢ ያሉ ወገኖቻችን ሲገፉ መጀመሪያ ድምጽ የሆነ፣ በደቡብ ወገኖቻችን ዘንድ ግፍ ሲበዛ ድምጽ የሆነ፣ በሰሜን ህዝቦች ዘንድ ችግር ሲኖር ድምጽ የሆነ፣ በምስራቅ፣ በምእራብ ላለው ኢትዮጵያዊ በየጊዜው ድምጽ የሆነ ፓርቲ ነው። አሁንም በኢትዮጵያ ውስጥ እኩልነት ሰፍኖ፣ የንጋት ኮከብ በኢትዮጵያ ውስጥ አስኪወጣ ድረስ ሃገራዊ ፓርቲ ሆኖ ትግሉን ለመቀጠል ከመቼውም ጊዜ በላይ ቆርጦ የተነሳን ድርጅት የምንደግፍ የሰሜን አሜሪካ የባልደራስ ደጋፊዎች የሞራል ልእልና እንዲሁም ኩራት ይሰማናል። መንግስት የይስሙላ ምርጫ አድርጎ የድሆችን ድምጽ ነጥቆ በደሉን ቀጥሏል። ይሁን እንጂ ባልደራስን ይዘን ትግላችንን ቀጥለን ሃገራችንን ወደ ዴሞክራሲና ወደ ልማት ወደ ሰላም ለመውሰድ የማንፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም። ድል ለዴሞክራሲ እስኪሆን ትግላችን ይቀጥላል። ነሃሴ 8፣ 2014 ዓመተ ምህረት የባልደራስ ድጋፍ በሰሜን አሜሪካ

Source: Link to the Post

Leave a Reply