መሪ እና ተጠያቂነት አሻራ ታህሳስ 23፣ 2013ዓ.ም) የወጋችን መነሻ ወደ ካናዳ ተጉዘናል፡፡ ካናዳ ኦንታሪዮ ግዛት ላይ በሀሳብ ተሰይመናል፡፡ ምን ሆነ መሰላችሁ የኦንታሪዮ የገንዘብ ሚኒስት…

መሪ እና ተጠያቂነት አሻራ ታህሳስ 23፣ 2013ዓ.ም) የወጋችን መነሻ ወደ ካናዳ ተጉዘናል፡፡ ካናዳ ኦንታሪዮ ግዛት ላይ በሀሳብ ተሰይመናል፡፡ ምን ሆነ መሰላችሁ የኦንታሪዮ የገንዘብ ሚኒስት…

መሪ እና ተጠያቂነት አሻራ ታህሳስ 23፣ 2013ዓ.ም) የወጋችን መነሻ ወደ ካናዳ ተጉዘናል፡፡ ካናዳ ኦንታሪዮ ግዛት ላይ በሀሳብ ተሰይመናል፡፡ ምን ሆነ መሰላችሁ የኦንታሪዮ የገንዘብ ሚኒስትር ለመዝናናት ወደ ካሪቢያ ደሴት ያመራሉ፡፡ አዲስ ዓመትም እና የገና በዓልም ስለሆነ መዝናናት የወግ ነው፡፡ ወጉ ቀረና ግን የኮቪድ ወረርሽኝ ስላለ ሚኒስትር ሆነው መዝናናታቸው በነውርነት እና በግዴለሽነት አስፈረጃቸው፡፡ ከስልጣናቸውም ለቀቁ፡፡ ህዝቤ በኮሮና እየተሰቃየ እኔ መዝናናቴ ሞኝ እና ጅላጅል ነኝ አሉ፡፡ ተፀፀተው ስልጣን ለቀቁ፡፡ በእርግጥ ካናዳን ከኢትዮጵያ ጋር ማወዳደር ቢከብድም ስለኛ መሪዎች ስብዕና ግን ሰውነት እንደ አቻ መስፈርት ተጠቅመን ለመርመር እንሞክራለን፡፡ 1) ኦሮሚያ ክልልን የሲኦል ምድር ያደረጉ አመራሮች ዛሬም ነፍጠኛን ሰብረነዋል እያሉ አሉ፡፡ እነዚህ አመራሮች የጊዲዮን 500ሺ ህዝብ አፈናቅለዋል፡፡ ብዙዎችን ገድለዋል፡፡ በሀጫሉ ሞት ከ120 ሰው በላይ ሲገደል ታዛቢ ነበሩ፡፡ ከዛሬ እስከ ትናንት በወለጋ ሰው እየሞተ ነው፡፡ በአንድ ቀን ብቻ ከ200 ሰው በላይ የታረደበት ጊዜ አለ፡፡ ዛሬም ኦነግ ጦር እያሰለጠነ ደቡብን፣ ሀረርን፣ ቢሻንጉልን፣ ጋምቤላን ለመውረር ተዘጋጅቷል፡፡ የኦነግ ጦር ከመንግስት ሲበልጥ ዝም ብለው ንፅሃንን የሚያስገድሉ ዛሬም እንዳሉ አሉ፡፡ 2) ከመተከል ህዝብ 50 ከመቶው ሲፈናቀል፣ሲሞት የተባበሩ ዛሬም አሉ እንዳሉ፡፡ 3) ህወኃት አብጦ መከላከያውን ሲዋጋ እና ሲያወድም፣ለጦርነት የዳረጉ ሰነፍ መሪዎች ዛሬም አሉ፡፡ 4) ሱዳን በሀገር ሉዓላዊነት ስትጥስ ፀጥ ያሉ መሪዎች ዛሬም መሪ ናቸው፡፡ 5) የህወሓት ስር ተክለው ዛሬም የህወኃት ውርስ አስቀጣይ መሪዎች ሀገሪቱን እያወደሙ አሉ፡፡ በዚህ መሃል የፖለቲካ ልሂቃኑ በብሄር እና በጎጡ ፣በአንደበት እየታመነ ፣ በውሸት እያጨበጨበ አለ፡፡https://www.youtube.com/channel/UCsfBw4xrhJzdMTzhWk_uX2A…

Source: Link to the Post

Leave a Reply