መሬት ለንቨስትመንት ዋነኛ ማነቆ ሆኗል ተባለ።የመሬት ችግር በኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንቱ ዋነኛ ማነቆ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለፀ።ባለሀብቱ በስፋት መወአለ ንዋዩን…

መሬት ለንቨስትመንት ዋነኛ ማነቆ ሆኗል ተባለ።

የመሬት ችግር በኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንቱ ዋነኛ ማነቆ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለፀ።

ባለሀብቱ በስፋት መወአለ ንዋዩን ሀገሪቱ ላይ እንዳያፈስ የመሬት ችግር ተግዳሮት እንደሆነበት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተወካይ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል።

ባለሀብቶቹ የሚያነሷቸውን ቅሬታዎችን እንደሚቀበሉ ያነሱት ተወካዪ በተለይም ከመሬት ጋር የተያያዘው ቅሬታ አሁንም እንዳለ አንስተዋል።

የአውሮፓ ህብረት ያጠናውን የመሬት ችግሮች ጥናትን እንደመንግስት እንደሚቀበሉት የሚያነሱት ሀላፊው በተለይም ግልፅ የሆነ መዋቅሮችን መፍጠር የሚያስችል ስርዐት ለመፍጠር እንደሚጥሩም አንስቷል፡፡

በኢንድስትሪ ፓርኮች ውስጥ የለማ መሬት የማግኘት ችግር እንደሌለ ያነሱት ሀላፊው ፤
ከኢንድስትሪ ፓርኮች ውጭ ስላለው የመሬት ጥያቄ ግን ሀገሪቱ በምትከተለው የፌድራሊዝም ስርዐት የመሬት አስተዳደር ስልጣን ለየክልሎች የተሰጠ በመሆኑ ወጥ የሆነ አሰራር አለመኖሩ አንደኛው ምክንያት እንደሆነም ገልፀዋል።

ተወዳዳሪ የሆነ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ መሬት ዋነኛው እንደሆነ የሚያነሱት ተወካዪ አሁንም ያሉብንን ችግሮች መለስ ብለን ማየት ይኖርብናል ሲሉም አንስተዋል።

የአውሮፓ ቻምበር ባለሀብቱ ከኢንድስትሪ ውጪ ያሉ መሬቶችን ለማግኘት የሚያጋጥሙ ውጣ ውረዶችን የሚያሳይ ሰነድ ይፋ ማድረጉን መዘገባችን የሚታወስ ነው።

በለአለም አሰፋ

መጋቢት 04 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply