መርማሪ ቦርዱ ጉዳት ለደረሰባቸው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የሚደረገውን የህክምና እርዳታ ተመለከተ

መርማሪ ቦርዱ ጉዳት ለደረሰባቸው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የሚደረገውን የህክምና እርዳታ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም የሚመረምረው ቦርድ በጦር ኃይሎች አጠቃላይ ሆስፒታል ተገኝቶ ጉዳት ለደረሰባቸው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ተገቢ የህክምና እርዳታ እየተደረገ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

መርማሪ ቦርዱ የማጣራት ስራውን አዲስ አበባ በሚገኘው የጦር ኃይሎች ሆስፒታል ተገኝቶ ያከናወነ ሲሆን፤ ከሆስፒታሉ የስራ ኃላፊዎችና የህክምና ባለሙያዎች ጋር በህክምና አሰጣጡ ዙሪያ ውይይት ማካሄዱ ነው የተገለጸው፡፡

የቦርዱ አባላት በሆስፒታሉ የተለያዩ ክፍሎች ተዘዋውረው በህክምና ላይ የሚገኙ የሰራዊቱን አባላት ማነጋገራቸውም ተጠቅሷል፡፡

ሁሉም ታካሚዎች ተገቢ የህክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑንና የምግብ አቅርቦትም በተገቢው መንገድ እያገኙ ስለመሆኑ ለመርማሪ ቦርዱ አባላት ተናግረዋል፡፡

በሚደረግላቸው የህክምና እርዳታና እንክብካቤም አብዛኞቹ ታካሚዎች እያገገሙ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የመርማሪ ቦርዱ አባላት ታካሚዎቹን በጎበኙበት ወቅት ስላደረጉት ተጋድሎና መስዋዕትነት ለሰራዊቱ አባላት ያላቸውን አድናቆትና ምስጋናም አቅርበዋል፡፡

ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የህክምና ድጋፍ እያደረጉ የሚገኙት የጦር ሃይሎች አጠቃላይ ሆስፒታል የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሀገራዊ ግዴታቸውን በአግባቡ እየተወጡ መሆኑን የመርማሪ ቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ ገልጸዋል፡፡

አቶ ለማ ይህ አኩሪ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ማሳሰባቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

The post መርማሪ ቦርዱ ጉዳት ለደረሰባቸው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የሚደረገውን የህክምና እርዳታ ተመለከተ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply