You are currently viewing መርሳ-ሓብሩ ======= ሃሳብን በሃሳብ ማሽነፍ የተሳነው የኦሮሞ መራሹ ስርአት እስከ ቀበሌ አፈናውን ቀጥሎበታል። ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከጀግናው የአማራ ከልዩ ሃይ…

መርሳ-ሓብሩ ======= ሃሳብን በሃሳብ ማሽነፍ የተሳነው የኦሮሞ መራሹ ስርአት እስከ ቀበሌ አፈናውን ቀጥሎበታል። ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከጀግናው የአማራ ከልዩ ሃይ…

መርሳ-ሓብሩ ======= ሃሳብን በሃሳብ ማሽነፍ የተሳነው የኦሮሞ መራሹ ስርአት እስከ ቀበሌ አፈናውን ቀጥሎበታል። ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከጀግናው የአማራ ከልዩ ሃይል መዋቅር መፍረስ ጋር ተያይዞ የመርሳ ህዝብ ስሜቱንና ተቃውሞን ገልጾ ነበር። አንዳንድ የስርአቱ ተላላኪዎችም ህዝቡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ አልፏቸው የነበረ ቢሆንም በከተማችን የፖለቲካ ሁኔታ የተቃውሞ የነቃ ተሳትፎ የሚያደርጉትን ለማስደንገጥ፡ለመጉዳትና የተቃውሞ ሃሳባቸው ስላስፈራቸው ብቻ መንገድ እንድዘጋ አድርጋችኋል በሚል ሰበብ አስረዋቸዋል። 1ኛ, የታላቁ መርሳ ሃይስኩልና ፕሪፓራቶሪ ርእሰ መምህር፡ ላመነበት ሁሉ ወድኋላ የማይለው የነ ፋኖ ዳናኤል አስረስና ፋኖ ሲላምላክ ወንድም ጀግናው ተመስገን አስረስን 2ኛ, የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ የመርሳ ሃብሩ ሰብሳቢ ፡መምህር አማረ ተገኘን፡ አማረ ተገኘ በተቃውሞው ጎራ በመሰለፍ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄን በመወከል ለመርሳ ሃብሩ የተወዳደረ፡ ያለ ምንም በጀት፡ደመወዙን ብቻ በመጠቀም፡ በሚሊየን በጀት የሚቀሳቀሰውን የ2 ወረዳ(ሃብሩና መርሳ ከተማ) ብልጽግናን ያንቦቃቦቀ፡ያስጨነቀ፡ ብዙ ፈተና ቢያደርሱበትም ማነንም ሳይሰማ የተወዳደረ ጀግና ነው። 3ኛ, ተመስገን ታደሰ(ፖሊስ የነበረ፡ አሁን መርሳ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ውስጥ የሚሰራና እነ ግርማ ሞገስን ወዘተ ንቁ ልጆችን እየለቀሙ እያሰሩ ነው። 4ኛ, ፋኖ ታሪኩ ጉበና 5ኛ, ፋኖ አባ ሽፈሬ ደሊል( እድሜው 76 ዓመቱ) 6ኛ, መምህር አጥናፉ ተገኘ 7ኛ, ወጣት ጊርማ ሞገስ 8ኛ, ፋኖ ሞላ ታቸው 9ኛ, መምህር ፍሰሃ ደምሴ 10ኛ, ፋኖ አያሌው ስጦት እና ሌሎችም የፋኖ አባላትና የማህበረሰን አንቂዎች ከ16/08/2015 ዓ.ም ጀምሮ ወልዲያ ማረሚያ ቤት ታስረው ይገኛሉ። በመሆኑም ለ17 ቀናት ያክል ፍ/ቤት ያልቀረቡ ሲሆኑና የናንተን ጉዳይ እኛ መክሰስ አንችልም በሚል ምክኒያት እየተሰቃዩ ይገኛሉ ብለዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply