መርካቶ ምጣድ ወይም ጋዝ ተራ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል።ኢትዮ ኤፍ ኤም ከአዲስ አበባ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ…

መርካቶ ምጣድ ወይም ጋዝ ተራ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም ከአዲስ አበባ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንዳረጋገጠው አደጋው ዛሬ ከረፋዱ 3:45 አካባቢ የተከሰተ ሲሆን እስካሁንም ገና ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አልዋለም።

አደጋዉ እንዳይዛመት ማድረግ ግን ተችሏል ብለውናል።

17 የድንገተኛ አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎች እና 85 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አደጋውን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ተብሏል።

አካባቢው ለአደጋ ተጋላጭ ነው በሚል የተለዬ እንደነበርም አቶ ንጋቱ ነግረውናል።

አካባቢው ተቀጣጣይ ነገሮች በብዛት የሚገኙበትና ቤቶችም ከእንጨትና ቆርቆሮ የተሰሩ መሆናቸው አደጋው ከፍ እንዲል ሲያደርግ ለትራንስፖርት እንቅስቃሴም አስቸጋሪ መሆኑን ነግረውናል።

የአደጋው መንስኤና ያደረሰው ጉዳት ገና ያልተጣራ ሲሆን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም አቶ ንጋቱ ገልጸዋል።

በሙሉቀን አሰፋ

ግንቦት 14 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply