መስከረም አበራ ከእስር ተለቀቀች

https://gdb.voanews.com/03370000-0aff-0242-1bd0-08daef602814_tv_w800_h450.jpg

ለሦስት ሳምንታት በእስር ላይ የቆየችው የ”ኢትዮ ንቃት” የዩትዩብ ሚድያ አዘጋጅ መስከረም አበራ ከእስር መለቀቋን ጠበቃዋ ሰለሞን ገዛኸኝ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት መስከረም አበራ በዋስ ከእስር እንድትለቀቅ የሰጠውን ትእዛዝ ተከትሎ ከእስር መፈታቷ ታውቋል።

በሌላ በኩል “በሕዝብ ደህንነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል ለመፈፀም እና ጥላቻ፣ አመፅ:፣ ሁከትና ብጥብጥን ለመቀስቀስ በማሰብ ተንቀሳቅሳለች” በሚል ከሥራ ባልደረባዋ ጋራ ክስ እንደተመሰረተባት ጠበቃዋ ጨምረው ገልፀዋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

Source: Link to the Post

Leave a Reply