መስከረም 07/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ) የአማራ ፋኖ አመራሮችና አባላት ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ ። በውይይቱም ክቡር አቶ አገኘው ተሻገር የአ…

መስከረም 07/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ) የአማራ ፋኖ አመራሮችና አባላት ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ ። በውይይቱም ክቡር አቶ አገኘው ተሻገር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዜዳንት ፣ ክቡር አቶ ገጹ አንዳርጋቸው የጠቅላይ ሚስትሩ የደህንነት አማካሪ ሚኒስቴር ፣ ክቡር አቶ አብርሃም አለኸኝ የብልጽግና ድ/ቤት ኃላፊ ፣ ክቡር ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ የሠላምና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊና የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ… እና በተለያየ የሰራ ኃላፊነት ያላቸው የክልሉ ከፍተኛ የፀጥታ አመራሮች በተገኙበት ከአማራ ፋኖ መሪዎችና አባላት ጋር በባህርዳር ከተማ ውይይት ተደረገ ። የውይይቱ ዓላማ የትግራይ ወራሪ ሃይል በአማራ ክልል ላይ ያደረገውን ወረራና በህዝባችን ላይ እያደረሰ ባለው ሰቆቃ ለመታደግ በፍጥነት ከአማራ ግዛት ውስጥ ሳይወጣ ሙሉ ለሙሉ መደምሰስ እና ጠላት ለአማራና ለኢትዮጵያ ልዑላዊነት ስጋት በማይሆንበት ደረጃ ማድረስ ያለመ ነው :: ለዚህም ትክክለኛው የችግር መውጫ በር እንደ አማራ ውስጣዊ አንድነት መገንባትና ተግባቦት ፣ የአሸናፊነት ስነ- ልቦና ከፍታ ከመላበስ ያለፈ ሌላ መፍትሄና መድሃኒት እንደሌላው ተብራርቷል ። የአማራ ፉኖ ልክ እንደ ትናቱ ቀደምት አባቶቻችን ሲወርድ ሲዋረድ ከኢትዮጵያ የታሪክ ድርሳናት የሚመዘዘውን :- – ፋኖነት ለአማራና የኢትዮጵያ የአንድነት ቋሚ ምሰሶ ፣ – ፋኖነት የጀግንነትና አርበኝነት ቀንዲል ፣ – ፋኖነት ለኢትዮጵያውያን ብሎም ለአፍሪካ ጥቁር ህዝቦች የአሸናፊነት ተምሳሌት ፣ – ፋኖነት ለተበደሉ ህዝቦች ራሱን መስዕዋትነት አድርጐ የአማራን ህዝብ ክብርና ነጻነት በማስጠበቅ ለኢትዮጵያ አንድነት ዘብ የሚቆም ፣ – ፋኖነት ስለ ህዝብ ፍትህና ነጻነት ብሎ ውድ ህይወቱን በበጐ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮጵያ የቍረ ጥ ቀን ልጅ እንደሆነ በተሳታፊዎችና በመድረክ መሪዎች በኩል በሰፈው ተነስቷል :: በመሆኑም ጁንታው በአማራ ክልል ውስጥ ባካሄደውን ወረራ ለመከላከልና ለመደምስስ በተካሄደው የጦርነት አውደ ግንባር ከመከላከያ፣ አማራ ከልዩ ሃይል ፣ ከአማራ ከሚሊሻ ና ሌሎች ሃይሎች ጋር በመቀናጀት የአማራ ፋኖ በተግባር በእሳት የተፈተኑ ጠላትን መቆሚያና መቀመጫ ያሳጡ እንቁ የፋኖ መሪዎችና አባላት በዘመኑ እንደተፈጠሩ በመድረኩ ተወስቷል። በመሆኑም ፋኖነትን ከአባቶታቸው የውርስ ካባ የደረቡ ጀግኖች እየተፈጠሩ መሆናቸው ነገሞ እልፍ አላዕፍ መሆናቸው አይቀርም :: በሌላ በኩል የጥይት ባሩድ ሳይሽታቸው በርቀት ብቻ በጦርነቱ ውስጥ ጀብዱ እንደሰሩ በማስመስል የፌስ ቡክ አርበኞችና ፎቶ ተነስቶ በመለጠፍ የሚቀነቀንላቸውና እንዲዘመርላቸው የሚፈልጉ ግለሰቦችም እንዳሉና በእውነተኛው የፍኖ መጠሪያ ስም የሚነግዱ ግለሰቦች መታረም እንዳለባቸው ተብራርቷል :: ስለሆነም በስቃይ ውስጥ ያለውንና የተዋረደውን የአማራ ህዝባችን ነፃ ለማውጣትና ኢትዮጵያን ለመታደግ እያንዳንዱ የፋኖ መሪና አባላት ከመንግስት ጐን በመሆን በራሱ ዕዝ እየተመራ ከፌደራልና ከክልል የፀጥታ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት በጠላት ላይ ኃያል ክንዱን ለማሳረፍ የጋራ ስምምነት ተደርሷል:: በጦርነት አውደ ግንባር የሚሰለፉ የፋኖ አባላትን ለሚደርሰባቸው ጉዳትም በመንግስት በኩል ድጋፍና ክትትል እንደሚ ደረግላቸው ቃል የተገባ ሲሆን የአማራ የፋኖ አባላትም ለአማራ ህዝብ ክብርና ነጻነት ሲባል ከመንግስት ጋር በመሆን የማይከፈል ዋጋ እንደማይኖር ባወጡት የአቋም መግለጫ አስቀምጠዋል ሲል የአማራ ክልል ሠላምና የህዝብ ደህንነት ጉዳዬች ቢሮ አስታውቋል ። አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን

Source: Link to the Post

Leave a Reply