You are currently viewing «መስከረም 12, 2015 ዓ.ም ከጠዋት 12:00 ሲሆን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በወረዳው የሚገኙ የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ በተጠና አኳኋን መጨፍጨፍ' ጀመሩ። ጭፍጨፋው' ቀጠለ ከቀኑ 7፡00…

«መስከረም 12, 2015 ዓ.ም ከጠዋት 12:00 ሲሆን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በወረዳው የሚገኙ የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ በተጠና አኳኋን መጨፍጨፍ' ጀመሩ። ጭፍጨፋው' ቀጠለ ከቀኑ 7፡00…

«መስከረም 12, 2015 ዓ.ም ከጠዋት 12:00 ሲሆን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በወረዳው የሚገኙ የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ በተጠና አኳኋን መጨፍጨፍ’ ጀመሩ። ጭፍጨፋው’ ቀጠለ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ሲሆን በገጠራማው አካባቢ ያለውን ጨርሰው ወደ ወረዳዋ መናገሻ ጃርቴ ከተማ ገቡ። በከተማዋ የሚገኙ አማራዎችን እጅግ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ጨፈጨፉ!! 60 አባወራዎችን በአንድ ቤት ዘግተው በእሳት አቃጠሏቸው» ********************************* ወለጋ ዞኖች በንጹሃን ላይ ያነጣጠረ ጭፍጨፋ ሪፖርት (በ4 አመት ዉስጥ) (በሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች) የአማራ ሚዲያ ማእከል መስከረም 21 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ 1. የወለጋ ነዋሪዎች ከ4 አመት በፊት በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞኖች ኦሮሞዉ ከአማራዉ እንዲሁም ሌሎች ብሔሮቻ ጋር በሀዘንም ሆነ በደስታ በመተጋገዝ በሰላም እና በፍቅር አብረዉ ኑረዋል፡፡ ኦሮሞ ከአማራ፣ አማራ ከኦሮሞ ጋር ተጋብቶ ተዋልዷል፡፡ ነግር ግን ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ኦነግ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር በመቀላቀል አማራ ኦሮሞን እንዲህ አድርጎ ሲጨቁን ነበር በማለት የተሳሳተ ቪዲዮ በማሰራጨት እና በማሰማት እንድሁም በማስተማር ወጣቱ በስሜት እንዲቀላቀላቸዉ አደረጉ፡፡ ከዛ በመቀጠል ንፁሃንን አግተዉት ብር መጠየቅ፣ መግደል፣ ንብረታቸዉን መዝረፍ እና ማፈናቀል ጀመሩ፡፡ 2. የወለጋ ንፁሃን ዜጎች ሰቆቃ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች የሚገደሉት ዜጎች፡-  አማራዎች በማንነታቸዉ ይገደላሉ  የኦነግ ቀላቢ እና ተባባሪ ያልሆኑ ኦሮሞዎች ይገደላሉ  ከአማራ የተወለዱ (የተቀላቀሉ) ኦሮሞዎች ይገደላሉ  የኦነግ ተባባሪ ያልሆኑ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል እና ፖሊስ ይገደላሉ  የኦነግ ተባባሪ ያልሆኑ የዞን፣ ወረዳ፣ ቀበሌ አስተዳደሮች ይገደላሉ  የኦነግ ተባባሪ ያልሆኑ ካቢኔዎች እና የብልፅግና አባሎች ይገደላሉ  የሀገር መከላከያ ሰራዊት ይገደላሉ የኦነግ ሸኔ ሰራዊት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በትንሹ ከ20,000 ያላነሱ ንፁሃን የአማራ ሴቶችን፣ ህጻናትን እና አቅመ ደካሞችን በስለት፣ በከባድ መሳሪያ እና በነዳጅ አርከፍክፎ በማቃጠል አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሞባቸዋል። እንድሁም ብዙዎች ቆስለዋል፣ አካለ ጎደሎ ሁነዋል፣ ከሞት የተረፉት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ህይወታቸዉን ለማዳን ከሞቀ ቦታቸዉ ተፈናቅለዉ በአቅራቢያቸዉ ወደሚገኝ ከተሞች ተሰድተዋል፡፡ በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ንፁሃን ዜጎች በቦታቸዉ ሁነዉ ህይወታቸዉን ለማዳን ለኢትዮጲያ መንግስት፣ ለክልሉ መንግስት፣ለዞን አስተዳደሮች፣ ለወረዳ አስተዳደሮች፣ ለቀበሌ አስተዳደሮች፣——- ወዘተ የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ብቻቸዉን እየተፋለሙ ይገኛሉ፡፡ አጋምሳ እና ሆሮ ቡሉቅ በተመለከት የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) እና ኩሽ ሚዲያ ኔትወርክ (KMN) የሚያናፍሱት እዉነታ እንደሚከተለዉ ይሆናል፡- 2.1. አጋምሳን በተመለከተ በአካባቢዉ የሚኖሩ አማራዎች ተፈናቅለዉ ሲሄዱ አጋምሳ ለ6 ወራት ኮማንድ ፖስት ስለነበረ የአጋምሳ ከተማ አማራ ነዋሪዎች ከቦታቸዉ አልተፈናቀሉም፡፡ ኮማንድ ፖስቱ ከአካባቢዉ እንደወጣ ነሐሴ 22, 2014 ዓ.ም ኦነግ ጃል ፈቀደ የሚመራዉ ሰራዊት ከተማዋን በመቆጣጠር ወደ 43 የሚጠጉ አማራዎችን ገደሉ፣ አገቱ እና ሌሎችን ለማቃጠል ቤት ዉስጥ ቆለፉባቸዉ፡፡ እንድሁም የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በኦነግ ተዘረፈ፣ ወደመ፡፡ ኦነግን አንቀላቀልም ያሉትን የኦሮሞ ሚሊሻዎች መሳሪያ ዘረፉ፡፡ በከተማዉ የታገቱት እና የሚጨፈጨፉት ንፁህን አማራዎች ለሚመለከተዉ አካል ቢጮሁም ሰሚ አላገኙም!! ነሐሴ 23, 2014 ዓ.ም ኦነግ ጃል ፈቀደ የሚመራዉ ሰራዊት በቤት ዉስጥ የተዘጋባቸዉን አማራዎች ለመጨፍጨፍ ሲሄድ በአካባቢዉ ለሚኖሩት አማራዎች ማለቃችን ነዉ ድረሱልን በማለት ጥሪ አደረጉ፡፡ ጥሪ የተደረገላቸዉ አማራዎች በየ አቅጣጫዉ እንደደረሱ ጃል ፈቀደ የሚመራዉ ሰራዊት ከተማዉን ለቆ ጠፋ፡፡ የከተማዉ የኦሮሞ ሚሊሻ በአማራዎች ላይ ተኩስ በመክፈቱ ብዙ ሰዉ ተጎዳ፡፡ 2.2. ሆሮ ቡሉቅን በተመለከተ በሆሮ ቡሉቅ የሚኖሩ 3 አማራዎች በማንነታቸዉ እጃቸዉን ወደ ኋላ በመሰር ተገድለዉ ከወና ቤት ዉስጥ ተጥለዉ በመገኘታቸዉ በተፈጠረ ግጭት የሞቱተን ነዉ፡፡ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN)፣ ኩሽ ሚዲያ ኔትወርክ (KMN) ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያ ጠል የሆኑ የባንዳ ሚዲያዎች በኦሮሚያ ውስጥ በሚኖሩ የአማራ ልጆች ላይ ግልጽ ጦርነት እንዲታወጅ ጥሪ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል። እንዲሁም ህይወታቸዉን ለማዳን ከባድ መሳሪያ ከታጠቀ ሀይል ጋር ብቻቸዉን እየታገሉ ባሉበት የድረሱልን ጥሪ ቢያሰሙም ተሰሚነት እንዳያገኝ አድርገዋል፡፡ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) እና ኩሽ ሚዲያ ኔትወርክ (KMN)፣—– ወዘተ ‹ፅንፈኛ የአማራ ታጣቂ እና ፋኖ በኢፊዲሪ መንግስት እና የአማራ ክልል መንግስት በመታገዝ በአማራ ክልል ፖሊስ መኪና ተጭኖ ድንበር አልፎ በመግባት ንፁሃን ኦሮሞን በክልላቸዉ ላይ ገደሉ፣ ንብረታቸዉን ዘረፉ፣ አፈናቀሉ፣ መሬታቸዉን ወረሩ› የሚል የተሳሳተ ዶኩመንት በማዘጋጀት ለኦነግ ሸኔ እና ለተባባሪዎች ጥሪ በማድረግ በሆሮ ጉዱሩ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች ከነሐሴ 22, 2014 ዓ.ም ጀምሮ ጉቶ ጊዳ ወረዳ ኡኬ ቀርሳ፣ አንገር ጉትን፣ አሙሩ ወረዳ፣ ሆሮ ቡሉቅ፣ ጃርቴ ጃርዴጋ፣ አጋምሳ፣ ሀሮ አዲስ አለም፣ ወዘተ የኦነግ ሸኔ፣ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል፣ የኦሮሚያ ፖሊስ እና ቄሮዎች’ በቁጥጥር ማዋላቸዉን ተከትሎ በስለት’ እና ከባድ መሳሪያ በመታገዝ በአማራዎች ላይ የዘር ማጥፋት ስራ እየተሰራ ነዉ። በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ በኦነግ የተገደሉ አማራዎች ቁጥር 385 ይደርሳል ሲሉ የአይን እማኞች ገለፁ። እስካሁን ድረስ ከ100 በላይ አስክሬን ሰብስበው እንደቀበሩ ገልፀዋል። አብዛኛውን አስክሬን ግን እስካሁን ድረስ ከለላ የሚሰጥ ታጣቂ ኃይል በመጥፋቱ መሰብሰብ እና መቅበር አልተቻለም ብለዋል። ከስፍራው መረጃ ያደረሱን አካላት። በኡኬ ቀርሳ ከ50 በላይ አስክሬን ሰብስበው እንደቀበሩ ገልፀዋል። በሶምቦ ጨፌ በኦሮሚያ ልዩ ሀይል በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ንፁሃን ላይ በተከፈተዉ ጦር ከ6 በላይ አስክሬን ሰብስበው እንደቀበሩ ገልፀዋል። በወለጋ ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ተልዕኮውን የጨረሰው የኦነግ ሰራዊት ወደ ሃሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ፣ አንገር ጉትን ከተማ፣ አሙሩ ወረዳ በስፋት እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ እዛ አካባቢ የሚኖሩ ንፁሃን አሁንም ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ወድቀዋል ተብሏል። ሀሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ ባለፈው አመት ከኦነግ ጭፍጨፋ ተርፈው የተጠለሉ ከ80 ሺ በላይ አማራዎች ይገኛሉ። እነዚህ አማራዎች የሚበሉትም ሆነ የሚለብሱት ምንም ነገር አለመኖሩን በቅርቡ ገልፀው ነበረ። በተጨማሪም አማራ ክልልን ከኦሮሚያ ክልል የሚያገናኘዉ መንገድ በመዘጋቱ ወዴትም መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን አሳውቀዋል። በወለጋ የአማራዎች ጭፍጨፋ በየጊዜው ሆን ተብሎ እንዲለመድ በመደረጉ ሚዲያዎችም ይሁን ማህበረሰብ አንቂዎች ትኩረት እየሰጡት እንዳለሆነ ተገልጿል። ይህ ደግሞ ሀዘኑን የበለጠ ልብ ሰባሪ አድርጎታል ተብሏል። የኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እንደገለፀዉ ወለጋ በንፁሃን ዜጎች ላይ ኦነግ፣ አማራ ኢመደበኛ ታጣቂዎች እና ሌሎች ጥቃት አድርሰዋል ብሎ ዘግቧል፡፡ ሌሎች ጥቃቱን የፈፀሙት እነ ማን ናቸዉ??? የኦሮሚያ ልዩ ሀይል? የኦሮሚያ ፖሊስ ? ቄሮዎች? የወለጋ አማራ ሚሊሻዎች ወገናቸዉን እና ለሀገራቸዉን ከጥላት ለማዳን የፀጥታ ሀይል በለለበት ብቻዉን ስለተጋፈጠ የአማራ ኢመደበኛ ታጣቂዎች እንደት ያስብለዋል??? ይሄን ብሎ የዘገበዉ የወለጋ አማራ ያለ ዘር እንዲያልቅ የፈለገ ነዉ፡፡ የአማራ ፋኖ እና ታጣቂ ድንበር አልፎ ወለጋ አልሄደም ። የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) እና ኩሽ ሚዲያ ኔትወርክ (KMN) የአማራ ፋኖ እና ታጣቂ ድንበር አልፎ ወለጋ ገቡ ብሎ የሚዘግቡት ከዚህ በፊት ከወለጋ ዞኖች ከሞቀ ቦታቸዉ ተፈናቅለዉ በአማራ ክልል በተለያዩ ቦታዎች የሚበሉትም የለላቸዉ፣ የሚለብሱት የለላቸዉ፣ መጠለያ ያላገኙት ኑሮ የሰለቻቸዉ ወለጋ የቀሩት ወገኖቻቸዉ ያለምንም ከልካይ እያለቁ በማየታቸዉ ህይወታቸዉን ለማዳን ተመልሰዉ የተቀላቀሉትን ይሆንል፡፡ 3. የወለጋ አማራ በማንናቱ ተጨፍጭፎ እንዲፈናቀል የተደረገበት አላማ በወለጋ የሚኖሩ አማራዎችን ጨፍጭፎ በማፈናቀል ንብረታቸዉን መዝረፍ ሲሆን አማራዎች መረጃ እንዳያወጡ እና እንዳይናበቡ በሚል ኔትወርክ በማዘጋት ሸኔ በአንድ በኩል የኦሮሚያ ልዩ ሃይሉ በሌላ በኩል ከበዉ ዉስጥ በማስገባት በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ንፁሃን አማራዎችን በአሰቃቂ ጨፍጭፎ ማፈናቀል፡፡ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባላት፣ የአባ ገዳ ሺማግሌዎች እና ካቢኔዎች በአንድ ሁነው አትንኩን አንነካችሁም በማለት ሸኔን ተማፅነው ስምምነት ማድረጋቸውን መረጃ ሳይታሰብ ሾልኮ ወጥቷል። 4.ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና ምስራቅ ወለጋ የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች በሚገኙ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት መቋረጡን የአካባቢው ነዋሪዎች በተለያዩ ሚዲያዎች እየተናገሩ ነዉ። እነዚህ ነዋሪዎች ጨምረው በተለያዩ ሚዲያዎች እና ፌስቡክ ፔጆች እንደተናገሩት የኢንተርኔት እና ዳታ አገልግሎት የመቋረጡ ምክንያት ንፁሃንን በነፃነት ለመጨፍጨፍ እንዲመቻቸዉ ነዉ ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአራቱም የወለጋ ዞኖች ማለትም ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ እና ምስራቅ ነዋሪዎች አስጊ ሁኔታ ላይ ናቸዉ። ይህ ጭፍጨፋ እና ዝርፊያ ሲፈፀም የኔትወርክ አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆን በአካባቢውም የፀጥታ ኃይል የሌለ መሆኑን ገልፀዋል። ቀኑ መስከረም 11, 2015 ዓ.ም ነው ። ቦታዉ ደግሞ ወለጋ ጃርዴጋ ወረዳ ነው። የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ወረዳውን እንደከበበ ይሰማል። ኦሮሞ ከቦታዉ ለቆ እንዲወጣ ተደረገ፡፡ በዚያ የሚኖሩ አማራዎች ጭንቅ ላይ ሆኑ። በዚያ ቅፅበት መብራትና ኢንተርኔት ጠፋ!! በህዝቡ ዘንድ ታላቅ መደናገጥ ተፈጠረ። በዚህ ሁኔታ ቀኑ መሸ። ሌሊቱን በጭንቀት አደሩ። መስከረም 12, 2015 ዓ.ም ከጠዋት 12:00 ሲሆን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በወረዳው የሚገኙ የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ በተጠና አኳኋን መጨፍጨፍ’ ጀመሩ። ጭፍጨፋው’ ቀጠለ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ሲሆን በገጠራማው አካባቢ ያለውን ጨርሰው ወደ ወረዳዋ መናገሻ ጃርቴ ከተማ ገቡ። በከተማዋ የሚገኙ አማራዎችን እጅግ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ጨፈጨፉ!! 60 አባወራዎችን በአንድ ቤት ዘግተው በእሳት አቃጠሏቸው። ከዚያም ወደ ወረዳ ማረሚያ ቤት በማቅናት ከዚህ በፊት ኦነግ ሸኔን ተዋግታችኋል ተብለው በማረሚያ ቤት ታስረው የነበሩ አማራዎችን ረሸኑ! በአንድ ቀን ብቻ በወረዳው የሚገኙ አማራዎችን ማፅዳት ቻሉ። በቁጥር 200 የሚሆኑ አማራዎች ተጨፈጨፉ። የቀረውም ቀየውን ለቆ ወደ አጎሬባች ወረዳዎች ተሰደደ!!! ሸኔ ከአማራ ያፀዳውን ወረዳዎች በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ማስተዳደር ከጀመረ ቆይቷል። የመንግስት ሀይልም ወደ ቦታው ለማቅናት አልሞከረም። አሁን የሸኔ ታጣቂዎች ዘመቻቸውን ወደ አጎራባች ወረዳዎች ለማስፋፋት እየተዘጋጁ ነው!! ወለጋ የሚላከዉ የፌደራል ፖሊስ (መከላከያ ሰራዊት) የንፁሃን ዜጎችን ህይወት ለምን አላዳኑም?? ንፁሃን ዜጎች ህይወታችንን አድኑን ብለዉ ጥሪ ሲያቀርቡ የመከላከያ ሰራዊቶች አለማዳናቸዉ፡-  ፈጣን ትዛዝ ስለማይሰጠዉ  እንደ ኦነግ ዘመንዊ መሳሪያ ባለመታጠቃቸዉ  ኦነግ ከህዝቡ ጋር በመቀላቀል እና በደፈጣ ስለሚያጠቃቸዉ 7. ወለጋ – በንፁሃን ደም የጨቀየች ምድራዊ ሲኦል! በኦሮሚያ ወለጋ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የሚፈፀመውን ማንነትን መሠረት ያደረገ ረፍት አልባ ፍጅት በተመለከተ ከመንግስት እና የመንግሥት ተከላካዮች የሚሰነዘሩ አስተያየቶች፦ ህሊናቸውን የሸጡት  ወለጋ ወለጋ አትበሉ! ይህ ታክቲካሊ ህወሓትን መተባበር ነው!  የህወሓት አጀንዳ እና ትኩረት ለማስቀየር የሚሠራው ሴራ ስለሆነ ዝም በሉ! በጣም የዘቀጡትና ከስብዕና በታች የሆኑት  ፋኖ ነው ጭፍጨፋ የፈፀመው!  ወለጋ ያሉት ጨፍጫፊዎች ኦሮምኛ ቋንቋ ለረዥም ጊዜ የተማሩ የህወሓት ወታደሮች ናቸው! መንግስት ደግሞ ላለፉት አራት አመታት ጭፍጨፋ በተፈፀመ ማግስት  አሸባሪው ሸኔ ሙሉ በሙሉ ተደመሠሠ!  አሸባሪው ሸኔ ወደ ጎረቤት ሀገር ፈረጠጠ!  አሸባሪው ሸኔ የተቆጣጠረው አንድም ቀበሌ የለም!  አሸባሪው ሸኔ የመንግስትን ጥቃት መቋቋም ተስኖት ተበተነ!  አሸባሪው ሸኔ እየፈረጠጠ ባለበት የፈፀመው ጥቃት ነው!

Source: Link to the Post

Leave a Reply